“የኢትዮጵያን ህዝብ አመሰግናለሁ” – ኮሎኔል ሻምበል በየነ
ኢትዮጵያ የምትኮራባቸው የክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ ራሳቸውን ሰውተዋል…ተገደሉ.. በሕወሓት ተማረኩ የሚሉ ዜናዎች እንደአዲስ ሰሞኑን ሲነገሩ ቆይተዋል። የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦችም በመደናገጥ ጠይቀውናል። ከሰሞኑ ከቆላ ተንቤን እስከ ጭላ የሕወሓት ኃይሎችን ሲደመሥስ ቆይቷል።
ይህ ጀግና ሰሜን ዕዝ በተጠቃ ጊዜ እግሩ ውስጥ ጥይት ቢገባም
• በሽጉጥ ገዳዮችን መትቶ ክላሽንኮቭ የማረከ፣
• በክላሽንኮቭ ተዋግቶ ብሬን የማረከ እና የውስጥ ባንዳ ከበባውን የሰበረ፣
• በብሬን(Bren) ተዋግቶ የትህነግ ልዩ ኃይል የከበባ ቀለበት የሰበረ፣
• ከትህነግ ልዩ ኃይል ከበባ ሰብሮ እንደወጣ ታንክ ላይ ወጥቶ በታንክ መዋጋት የቀጠለ፣
• በፈፀመው ጀብዱ ተስፋ ቆርጦ እና ግራ ተጋብቶ የነበረውን የተበታተነ ጦር አሰባስቦ እና አነቃቅቶ አንድ ቀን ከተዋጋ እና ካዋጋ በኇላ ቀስ እያለ ወደ ኤርትራ ያፈገፈገ፣
• ከእነ ጀኔራል አበባው ጋር ተገናኝቶ ከተነጋገረ በኇላ ጦሩን አደራጅቶ በመመለስ ከባድ ምሽጎችን እየደረመሰ ተንቤን ድረስ ትህነግን ያሳደደ፣
• ቆላ ተንቤን ድረስ ጦሩን ይዞ ወርዶ ትህነግን ሲያሳድድ የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ እና ሌሎች የታገቱ 1200 በላይ መኮንኖችን(ከከፍተኛ እስከ መስመር) ከእገታ ያስለቀቀ ጀግና ተዋጊ እና የተሟላ የጦር መሪን ሕወሓት ሊገድለው ብዙ ጊዜ ሞክሯል። ከሰሞኑም ለ6 ቀናት በተደረገው ውጊያ ከቦት የነበረ ቢሆንም በጀግንነት የከበባቸውን ደምሱኡአቸዋል። ታዲያ ሕወሓትትች ሞተ… ገደልነው… ማረጅነው እያሉ ቢያወሩ አይደንቅም።
ከፈጸማቸው ከባባድ ድሎቹ መካከል ብዙ ጀብዶች የፈጸመው ጀግናው ኮሎኔል ሻምበል በየነ በጀግንነት አሁንም በትግል ሜዳ ላይ መኖሩን ለሕዝብ ለመግለጽ በአጭሩ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ተዋቸው ደርሶ አነጋግሮታል። ብዙ ነገር ግልጽ የሚያደርገውን ቆይታ እነሆ። ሞተ… ተማረከ.. ተገደለ እያላችሁ በሚዲያ ያሰራጫሁትም እፈሩበት።