ተደራጅተው የመጡት የሕወሓት ታጣቂዎች በራያ ባላ እና በራያ ወፍላ በአማራ ልዩ ኃይል ተደመሰሱ
ህጻናትን ጭምር በማስታጠቅ ኮረምን ለመቆጣጠር የተንቀሳቀሰው የሕወሓት ታጣቂ በራያ ባላ እና በራያ ወፍላ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል መደምሰሱን ከስፍራው የመጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
በራያ አካባቢ ሕወሓት ከ5 ቀናት በፊት ውጊያ መክፈቱን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። ሕወሃት “ዘመቻ አሉላ አባነጋ” የሚል ስም በሰጠው በዚሁውጊያ ዋናው አላማው ኮረምን መቆጠር እንደነበር የተማረኩ እና እጃቸውን የሰጡ ታጣቂዎች ተናግረዋል። በራያ ባላ በኩል መጀመሪያ ለማጥቃት የመጣው ይኸው ቡድን በአማራ ልዩ ኃይል ተሸንፎ የተደመሰሰው ተደምሦሶ፣ የእጅ የሚሰጠው እጅ ሰጥቶ የቀረው ተበታትኗል ይላሉ ምንጩ። በዚህ አካባቢ ሽንፈት የደረሰበት የሕወሓት ቡድን እንደገና አቅጣጫ ቀይሮ ኃይል በመጨመር በወፍላ በኩልበማጥቃት ኮረምን ሊቆጣጠር አቅዶ የነበረ ቢሆንም የአማራ ልዩ ኃይል በርካቶችን በመደምሰስ የቀረው ሲበተን እጃቸውን የሰጡት በአሁኑ ሰዓት በአማራ ልዩ ኃይል እጅ እንደሚገኙ ምንጩ አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ደጀኔ አሰፋ ስለኮረሙ የሕወሃት እቅድ ሲዘግብ እንዲህ ብሏል።
ጣፋጭ ድል ከራያ ኦፍላ ኮረም!!!!
ሰሞኑን ከሃውዜን እስከ ቆላ ተንቤን: ከአገረ ሰላም እስከ
አግበ የጭላ: ከብዘት እስከ እንጥጮ እስከ ራማ ድረስ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ባካሄደው የአሰሳ ዘመቻ የተቀጠቀጠው የጁንታው ርዝራዥ ማምለጫ ሲያጣ እንደለመደው ጥሻ ለጥሻ በመሸሽ ሸጡን ተከትሎ ወደ አበርገሌ እና ወደ ኮረም ዙሪያ በመምጣት ተደብቆ ከረመ::
ዛሬ ሃሙስ ቀን የኮረም የገበያ ቀን ነው::
ታዲያ ጁንታው የዛሬውን ሃሙስ የኮረም የገበያ ቀንን በማስታከክ ሰርጎ ገቦችን ገበያተኛ በማስመሰል በማለዳ ወደ ኮረም ከተማ አስገባ::
ቀጥሎም የጁንታው ርዝራዥ ሃይል አድነባ ተብሎ በሚጠራው የኮረም ገጠር አካባቢ ጥይት መተኮስ ጀመረ::
ይህ ማለት በከተማ ውስጥ እና ከከተማ ውጭ ጥቃት በመክፈት ከእጁ የወጣውን የራያን ህዝብ ለመበቀል ያለመ ነበር:: መቼም ቢሆን የጁንታው ሃይል ከተማን ቀርቶ የገጠር ቀበሌን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቁመናም ሆነ ሞራል እንደሌለው በጣም ሊታወቅ ይገባል!!!! በማይካድራ እንደፈፀመው ሁሉ የራያን ህዝብ ለመበቀል ግን ሙከራውን ቀጥሏል::
ታዲያ ይህን የጁንታውን ሃሳብ እና እንቅስቃሴ የተገነዘበው የራያ ኦፍላ ኮረምን እና አካባቢውን እያስተዳደረ ያለው ኮማንድ ፖስት ሦስት ነገሮችን በአስቸኳይ አደረገ::
1ኛ) የዛሬው የኮረም ገበያ ዛሬ ጧት ሶስት ሰዓት ገደማ በፍጥነት እንዲፈርስ አደረገ
2ኛ) ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ አዘዘ:: ከገጠር ለገበያ የሚገባውንም ባለበት እንዲቆይ አደረገ::
3ኛ) ገበያው እንዲፈርስ እና ህዝቡ ወደ ቤት እንዲገባ ካደረገ በኃላ አድነባ አካባቢ የሽፍታነት ተግባር ሲፈፅም የነበረውን ርዝራዥ የጁንታ ሃይል ዛሬ ከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ጀግናው ሰራዊታችን አይቀጡት ቅጣት በመቅጣት የሞተው ሞቶ የተማረከው ተማርኮ የተረፈው ፈርጥጦ ወደ ዛታ እና ወደ ሰቆጣ መስመር ሸሽቷል!!!! የሙት ቁጥሩን በውል ማረጋገጥ ባልቻልም ተማርከው ወደ ወልዲያ የተወሰዱት ግን 29 መሆናቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠውልኛል!!!! የፀጥታ ሃይላችን ወታደራዊ የአመራር ብስለት : ለህዝብ ደህንነት ያለው ተጨናቂነት : ከህዝቡ ጋር ያለው ጥልቅ ግንኙነት እና ያካበተው ወታደራዊ ብቃት በቃላት የሚገለፅ አይደለም!!!!! ግሩም ድንቅ ተብሎለታል!!!!
ትላንትና ፍቅረ ወልዳ በተባለው የሰቆጣ መስመር ላይ ጁንታው ተመሳሳይ ቅጣት የተቀጣ ሲሆን ከሶስት ቀናት በፊት ደግሞ በራያ ባላ አካባቢ ታይቶ የነበረውን ርዝራዥ ሰራዊታችን እንዴት እንዳደረገው እዚህ መፃፍ ይቀፈኛል!!!! የጁንታው ተባራሪ ሃይል እሬሳቸውን መቅበር እንኳን ሳይችሉ ቀርተዋል!!!! በራያ ባላ ዙሪያ ሁሉም አመድ ሆነዋል!!!! ዛሬም በኮረም ዙሪያ በተደረገው አፋጣኝ ኦፕሬሽ ግማሽ ቀን ያህል እንኳን መዋጋት ሳይችል ጁንታው በርካታ ሙት : አያሌ ቁስለኛ እና ምርኮኛ ሆኖ የቀረው ጥቂቱ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ዛታ እና ሰቆጣ መስመር ፈርጥጧል!!!!! በጣም አሳዛኙ ነገር ጁንታው አሁን በወታደርነት የሚጠቀመው ታዳጊ ህፃናት ልጆችን ነው:: ከኪሳቸው የሚገኘው ደግሞ ሃሽሽ እና ቆሎ ነው:: ((መቼም አስከሬን መለጠፍ ከኢትዮጵያዊ ወግና ባህላችን ውጭ በመሆኑ አላወጣውም እንጅ እጄ ላይ በርካታ ፎቶዎች አሉ!!!)) በአጠቃላይ ግን የጁንታው መቀበሪያ ራያ ላይ ነው የሚለውን ትንግርት ልብ ይሏል!!!! ጁንታው ሁሌም ቆላ ተምቤን እና የተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ላይ ሲደቆስ እየፈረጠጠ ወደ ራያ ይወርዳል!!! ከዚያም ራያ ላይ አመድ ይሆናል!!!! የዛሬ ሶስት ወራት ገደማ በማይማእዶ በሺህ የሚቆጠር የጁንታው አስከሬን እንደተቆጠረ መግለፃችን ይታወሳል!!!! ትላንትም ትላንት ወዲያም ዛሬም ይሄው ሆኗል!!!!! እያዞረ እያሽከረከረ ወደ ራያ ያመጣቸዋል!!!! ፍፃሜያቸው ራያ ላይ ለመሆኑ እየታየ ይገኛል!!!! ጁንታው አለሁ ለማለት እዚህም እዚያም ሊያሸብር ቢሞክርም ምሱን እያገኘ በየጊዜው እያለቀና እየተመናመነ ይገኛል!!!! ጁንታው አሁን የቀረው የሚንተፋተፍ ምላሱ ነው!!!! እሱንም በቅርቡ ይውጥዋል!!!!