በአማራ ክልል አራት ከተሞች “ግሪን ሀውስ” የተባለ ድርጅት አዲስ ዘመናዊ መንደሮች ሊገነቡ ነው!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስር በሚገኙ አራት ከተሞች በክልሉ ባለሐብቶች በተቋቋመው “ግሪን ሐውስ” ድርጅት በ40 ቢሊዮን ብር ወጭ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮች ሊገነቡ ነው።
በባለሐብቶች የፕሮግራም ማስጀመሪያ ላይ የተገኙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሉ በሚገኙ ከተሞች የሚሰማሩ ለ96 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ መውሰዳቸውን ገለጸው አሁን ባለሐብቶቻን ለጀመራችሁት መልካም ተግባር የክልሉ መንግሥት ከጎናችሁ ሁኖ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል የመንደሮችን ግንባታ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በማድረግ ሀገራዊ ትስስር ልትፈጥሩ ይገባል ሲሉ
አቶ አገኘው አሳስበዋል ።
ዘመናዊው መንደሮች የሚገነቡት በባህር-ዳር ፣ ጎንደር እና ደብረ ብርሐን ኮንቦልቻ ከተሞች ሲሆን ለእያንዳንዳቸው 10 ቢሊዮን ብር ተደድቦላቸዋል።
በግሪን ሐውስ ድርጅ የሚገነቡት ዘመናዊ መንደሮቹ ሲኒማ፣ የመዋኛ ገንዳዎች ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ፣ የልጆች መዝናኛ እና የአዋቂዎች መዝናኛዎችን ያካተቱ ናቸው።
በተጨማሪም ከኬጂ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ ደረጃውን የጠበቁ ሆስፒታሎች እና ዘመናዊ ሆቴሎችም ይካተቱበታል።
“ግሪን ሐውስ” ከዘመናዊ መንደሮች በተጨማሪ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ፣ ለልማት ተነሽዎች ፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች በዝቅተኛ ክፍያ የመኖሪ ቤት አፓርታማዎችን በክልሉ በሚገኙ ከተሞች የሚገነባ ይሆናል
በመጀመሪያው ፌዝ በባሕር ዳር 2 ሽ አምስት መቶ ቤቶች ይገነባል
ለሁለት ሽ ወጣቶች የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሉዋል።
Tewachew Derso