ከሕወሓት ጁንታ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በአማራ ክልል ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ፅፅቃ ግንቦት 25/2013 ዓ.ም (ዝቋላ ኮሙዩኒኬሽን) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።


የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ በለጠ መስፍን እንደተናገሩት ግንቦት 22/2013 ዓ.ም በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎና ጥቆማ በአብርገሌ ወረዳ አዋሳኝ በሆነው በሰሜን በር ቀበሌ ላይ መኖራቸውን በህብረተሰቡ ጥቆማ የተሰጠ ሲሆን ከቦታው ለቀው በመንቀሳቀስ ተላ ወንዝ አከባቢ ሲደርሱ በወረዳው ፀጥታ ሃይል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል ።
እነዚህ ግለሰቦች በእጃቸው አንድ ክላሽ፣ ሁለት ቦንብ፣ 363 የክላሽ የጥይት ፣ 120 የብሬል ጥይት ፣36 የብሬል ሸልሸል እና 28,500 ብር ይዘው መቆየታቸውን ተናግረው፤ የተጠርጣሪዎቹ ቁጥር አምስት ሲሆኑ ሶስትቱን በቁጥጥር ስር ሲያውሉ ሁለቱ ማምለጣቸውን ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል ።
እነዚህ ግለሰቦች እንደ ፀጥታ መዋቅር ግምገማ ከአሸባሪው የህወሓት ጁንታው ቡድን ጋር ግኑኝነት ያላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል ።