በኦሮሚያ ክልል በገብረ ጉራቻ እና ፍቸ መሃከል ዛሬም የታጠቁ ሃይሎች አሽከርካሪወች ላይ ተኩስ ከፍተዋል መኪና አቃጥለዋል

በኦሮሚያ ክልል ፊቼ እና ደብረጉራቻ አካባቢ ባለችው አሊደሮ ከተማ ታጣቂዎች በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በሰላማዊ ሹፌሮች ላይ ጥቃት ሰነዘሩ።

ይህን ተከትሎ በኦሮምያ ክልል አሊደሮ በተባለው አካባቢ በደረሰው የመኪና መቃጠልና በሰዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ምክንያት ከአማራ ክልል ወደ አ/አበባ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መዋሉ ተገልጿል።


ትንናት ግንቦት በ14/09/13 ሌሊት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሊደሮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 1 ኤፍ ኤ ሳር መኪና በታጣቂዎች በመቃጠሉና በውስጡ ባሉ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ ምክንያት ከአማራ ክልል የሚንቀሳቀስ ማንኛውም መኪና እና መንገደኞች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ከደጀን ከተማ እስከ ኪዳንምረት ቤ/ክርስትያን ድርስ ባሉበት መቆማቸውን የደጀን ከተማ ኮምዩኒኬሽን አስታውቋል።
በቅርቡ ከ1 ወር በፊት እዚሁ አሊደሮ በተባለው ቦታ ላይ ከ 8 ያላነሱ ሹፊሮችና ረዳቶች በታጣቅዊቾ ጥቃት ሀብትና ንብረት ወድሞ ምንም መፍትሄ ባለመሰጠቱ አሁንም ትላንት ሌሊት መኪና ሲቃጠልና ሰዎች ላይ አደጋ ሲደርስ እያየን መንቀሳቀስ አንችልም። ከዚህ ቦታ የምንንቀሳቀሰው መንግስት የህዝባችንን ሞትና እልቂት ማስቆም ሲችል ነው ፡፡ በሚል ነው ሾፌሮቹ ደጀን ከተማ ለመቆም የተገደዱት ተብሊአ፤።
“እኛ ሹፊሮች ለሀገራችን ልማት የጀርባ አጥንት ለሆነው የትራንስፖርት አገልግሎት ደፋ ቀና እያልን በምንሰራበት ወቅት የምንታረድ፣ የምንሞት፣ ሀብትና ንብረታችንን የምንዘረፍ ከሆነና ለህይወታችንና ለንብረታችን ምንም ዋስታ ከሌለን ባለንበት በመቆም እራሳችንን መከላከል መርጠናል ፡፡ በተጨማሪም በርካታ መንገደኞች እየተፈጠረ ባለው ችግር ላይ በከፍተኛ ስሜት ፣ቁጭትና ምሬት ብሶታቸውን በስፋት ተናግረዋል ፡፡
በደጀን ከተማና ወረዳ የሚገኙ የፖሊስና የፀጥታ ሀይሎች መንገደኞችን በማነጋገር መንገዱ እንዲከፈትና የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲቀጥል ጥርት ቢደረግም መንገደኞች ፣ሹፌሮችና እርዳቶች ብሶታቸውንና ችግራቸውን በመናገር አሁንም ችግሩ እየቀጠለ ሊሄድ ስለሚችል መንግስት ለህይወታችንና ለንብረታችን ዋስትና ካልሰጠን መንቀሳቀስ አንችልም ብለዋል ፡፡
በመሆኑም ባሁኑ ሰዓት በደጀን ከተማና አካባቢው በርካታ መኪናዎች በመቆማቸውና ወደ አ/አበባ የሚደረግ እንቅሰቀቃሴ በመቆሙ እናቶችና ህፃናት፣አዛውንቶች የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች እየተጉላሉና ለእንግልት እየተዳረጉ ስለሆነ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ መልዕክታችን ነው ፡፡

የኦነግ ሸኔ የተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ኦሮሚያ ክልል አሊደሮ ከተማ ሾፌሮች ላይ ተኩስ ከፍተው ጉዳት አድርሰው መኪና ሲያቃጥሉ፤ ከ1ወር በፊት እዚሁ ቦታ 6 የሚሆኑ አሽከርካሪወች ህይወት ጠፍቷል። ከ2 ወር በፊት እዚህ ቦታ ወደ 3 አሽከርካሪወች መገደላቸው ይታወሳል።