ከአንድ ወር በፊት በጌታቸው ረዳ መንገድ መሪነት የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል አበርጌሌ ያደረሱት ውድመት ይፋ ሆነ
(ዘ-ሐበሻ) ከአንድ ወር በፊት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ሚያዝያ 17 ቀን ለ18 /2013 ንጋት 11: 00 ሰዓት አካባቢ የጁንታው ርዝራዥ የአበርገሌ ወረዳ ማእከል በሆነችዉ ኒየረ-አቁ ከተማ ሰርጎ በገባበት ወቅት ከቀጠፈብን ህይወት በተጨማሪ በቁሳዊ ሃብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ይፋ ሆነ።
የአበርገሌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ ወንድሙ ደመቀ እንደገለጹት እንደሚታወቀዉ ከዚህ በፊት ጁንታዉ የጻና ጤና ጣቢያን እንዲሁም የ07 እና የ04 ቀበሌ ጤና ኬላዎችን መድሃኒትና የተለያዩ ቁሶችን የዘረፈና ንጹሃንን የቀጠፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ያ አልበቃዉ ብሎ አሁን ደግሞ በከተማችን ገብቶ ጉዳት ሲያደርስ በአጸፋዉ እራሱ ጁንታዉ ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት በጀግናዉ ልዩ ሃይላችን የደረሰበትና የተሽመደመደ ቢሆንም ከቀጠፈብን ህይወት በተጨማሪ ኒራቅ ጤና ጣቢያ ላይና ከተማዉ ላይ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የገለጹ ሲሆን ይህም:-
1ኛ- ሰባት የመንግስት መኪኖች ማለትም የእናቶች ብሩህ ተስፋ የሆኑና ለማንኛዉም ሰባዊ እርዳታ አገልግሎት የሚሰጡ ሶስት አምቡላንሶችና አንድ ሲንግል ካፕ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ የወደሙ ሲሆን ሁለት ዳብል ካፕ መኪኖች ደግሞ በጥይት ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፥እንዲሁም አንድ አንቡላንስ ዝቅተኛ ጉዳት ደርሶበታል፥
2ኛ-በእናቶችና ህጻናት ላይ በስነ ምግብ ዙሪያ የሚሰራ ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድን/ዩኒሴፍ/በክራይ ሲሰራ የነበረ አንድ ኮብራ መኪና ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ ወድማል፥
3ኛ- ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር/ዋልታ ገጠር መንገድ ሲንግል ካብ መኪና ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ ወድማል፥
4ኛ- አንድ የግል ሚኒባስ በተመሳሳይ በጥይት ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል እንዲሁም አንድ የግል ባጃጅ መካከለኛ ጉዳት ደርሶባታል፥በተጨማሪም የሃዉስ ኮድ መኪና ዝቅተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
5ኛ- ጤና ጣቢያ ላይ አንድ ሙሉ ብሎክ ባለስድስት ክፍል ከነሙሉ እቃዉ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ የወደመ ሲሆን በዉስጡ የሃላፊና የጽሃፊ ክፍል÷የሰዉ ሃይል ክፍል ÷የንብረት ክፍል÷ፋይናንሻልና ሰነድ ክፍልና የተኝቶ ህክምና ክፍል ያካተተ ሲሆን ከነሙሉእቃቸዉ ወድመዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ከነሙሉቃዉ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን እንዲሁም የማዋለጃ ብሎክ ላይ ሁሉም ክፍሎች በተተኮሰ ጥይት በራቸዉና መስኮቶቻቸዉ ተብስተዋል፡፡ በተጨማሪም የወረዳዉ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በተተኮሰ ጥይት ተበሳስቷል ሲሉ በሪፖርቱ ላይ ተናገረዋል።
ጌታቸው ረዳ የዋግ ሕዝብ ሕዝባችን ነው፤ የትግራይ ሕዝብ አካል ነው እያለ ሲናገር ቆይቶ ታጣቅዊቾን እየመራ በመምጣት ይህን ሁሉ ጥፋት አድርሶ ተመልሷል ተብሏል። እነጌታቸው ከማህበራዊ ሚዲያ ይህን ሁለት ሳምንት የጠፉ ሲሆን የዚህም ምክንያቱ ከዚህ ቀደም ወደ አማራ ክልል አቅራቢያዎች እየመጡ ኢንተርኔት ስለሚጠቀሙ ነበር። አሁን ግን መከላከያው አካባቢውን በመቆጣጣሩና ትርፍራፊዎቹንም ጁንይታው አካላት ስላጸዳቸው ለጊዜው እነጌታቸው ተደብቀው ይገኛሉ ተብሏል።