ለአማራ ህዝብ መፈናቀልና መገደል ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ ሕገመንግስት እንዲቀየር በሚኒሶታ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተጠየቀ
የአማራ ህዝብ መገደልና መፈናቀል ይብቃ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በጠዋቱ በሚኒሶታ ስቴት ካፒቶል ደጃፍ በመውጣት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በስፍራው የሚትገኘው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንዳስታወቀችው በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች እየተሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለአማራ ህዝብ መገደል፣ መፈናቀል፣ መቁሰልና መገለል ምክንያት የሆነው ሕገመንግስት እንዲቀየር የሚጠይቀው ይገኝበታል።
“ለሃገር ሰላ ሲባል ያሳየነው ት ዕግስት እንደ ፍርሃት መቆጠር የለበትም”፤ ዕያንዳንዱ የክልል መንግስት በውስጡ ለሚኢሩ ዜጎች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት፣ የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ ለማውገዝ ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው፣ የአማራን ሕዝብ ነጥሎ ማጥቃት ይቁም የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን የያዙት ሰልፈኞቹ ለአሜሪካ መንግስት የሚኒሶታ ተወካዮችም ጥሪዎችን አቅርበዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ግድያ፣ መፈናቀል እና መገለል የሚያስረዱ መል ዕክቶችንም ለሚኒሶታ የሕዝብ ተወካዮች በደብዳቤ አስገብተዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በሚኒሶታ የአማራ ውርስና ቅርስ ማህበር ነበር።