የትህነግ ደጋፊዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ውጤት የሚያሳዝን ዜና ሆኖባቸዋል

የትህነግ ደጋፊዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት UNSC በኢትዮጵያ ጉዳይ የጠራው ስብሰባ ውጤት የሚያሳዝን ዜና ሆኖባቸዋል።

በዛሬው ዝግ ስብሰባ ካለውጤት ከተበተነ በኋላ በአንድ ሉላዊ ሃገር መንግስት የውስጥ ጉዳይ መግባት ሉዓላዊነትን መዳፈር መሆኑን የራሺያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል። ሩሲያ በስብሰባው ላይም ይህን አቋም የያዘች ሲሆን በተጨማሪ ቻይናና ህንድም ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷ ትፈታለች በማለት ጣልቃ ገብነትን ተቃውመው የሕወሓትን ተስፋ ገድለዋል።


የ ዕለቱ ዋና ዜናም ተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም / ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ስብሰባ ያለ ምንም ስምምነት ተጠናቀቀ የሚለው ሆኖል። ትህነጎችም ወደ ተለመደው የሃሰት ዜና ማሰራጨት በመሰማራታቸው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ የሞናሊዛ ቅጥፈት በሚል የጻፈውን ወቅታዊ ጽሁፍ አነብላችኋለሁ እስከመጨረሻው አብረን እንከታተለው።

ጸሐፊ፡ ክንፉ አሰፋ
አቅራቢ፡ ሔኖክ ዓለማየሁ