የፈንቅል አመራር የማነ ንጉሴ አሟሟት ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች ዘ-ሐበሻ እጅ ገቡ | ከፌደራል ፖሊስ እውቅና ውጪ የጁንታውን አመራር መኖሪያ ቤት ራሱ ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በህገ ወጥ መንገድ ለግል ጥቅም ፍለጋ ሲያስበረብር ነበር የሚል ክስ ከትግራይ ተወላጆች ቀርቦበት እንደነበር ተጋለጠ
ትጥቅ ያልፈታ የሕወሓት ትርፍራፊ ኃይል በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃቶችን እየሰነዘረ ከፖለቲካ ውጭ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን እየገደሉ መሆኑን በተደጋጋሚ ዘግበናል። አሁን ደግሞ የፈንቅል አመራር የማነ ንጉሥን መግደላቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቡ አይዘነጋም።
የማነ ተገደለ ተባለ እንጂ እንዴት ተገደለ የሚለው ጉዳይ ብዙም አልተሰማም። ዘ-ሐበሻ ከታማኝ መረጃ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከመገደሉ ጋር ተያይዞ የነበሩ ሁኔታዎችን ያሳያል።
በቀን 13/06/2013 ዓ.ም 4:00 ሰዓት አካባቢ ሟች አቶ የማነህ ንጉሱ ወደ ሄዋኔ ከተማ ወደ ቤተሰቦቹ ሶስት መከላከያ በመያዝ ከሄዴ በኋለ ከከተማው ዋናው አስፓልት ወደ ምዕራብ በኩል 500 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አዲስ ሰፈረ በተባለ አካባቢ ካለዕታ ገ/እግዚአብሔር የምትባል ጠላ ሻጭ ቤት በር ላይ ወጣቶች እንዲሁም ቤት ውስጥ ትጥቅ ያልፈቱ ሚሊሻዎች ባሉበት ሟቹ ከቭቲዝ መኪና ወርዶ በአካባቢው አንድ ት/ቤት ተዘርፎ ስለነበር በር ላይ ጠላ እየጠጡ የሚገኙ ወጣቶችን እናንተ እያላችሁ ት/ቤት እንደት ይዘረፋል በማለት እያናገራቸው እያለ ውስጥ ያሉ ሚለሻዎች ሰምተው ማነው የሚያወራው በማለት ሲጠይቁ የማነ ፈንቅል ነው ተብሎ ሲነገራቸው የማነም ንግግሩን ጨርሶ መኪናውን አስነስቶ መንቀሳቀስ ስጀምር ሚሊሻዎች ከቤት ውስጥ በመውጣት ቁም ስሉት ጉዞውን ስቀጥል ጥይት ተኩሰውበት እሱእና አንድ መከላከያ ከሞቱ በኋላ ሌሎች ሁለቱ የመከላካያ አባላት ከመኪና በመውረድ አንድ ሚሊሻ እና ጠላ ቤት አካባቢ ከነበሩት አንድ ወጣት የገደሉ ሲሆን እነሱም በሌሎች ምሊሻዎች ተገድሎዋል።
በአጠቃላይ በተኩስ ልውውጡ 6 ሰው የሞተ ሲሆን የየማነን አስከሬን ቤተሠቦች በመውሰድ እንደቀበሩት እና ሌሎችም በአቅራቢያው መቀበራቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይዘው የሄደውን መኪና አሰና ሰራዊቱ ታጥቀውት የነበረውን መሣሪያ ወዴት እንደገባ እንዳልታወቀ ፤ ከመቀሌ የተንቀሳቀሱ የምርመራ ቡድን አካባቢው ላይ ግጭት በመኖሩ ስለ ሟች ከላይ ከተገለፀው በላይ ምርመራውን መቀጠል እንዳልቻሉ መረጃ ሰጥተውናል።
በሌላ በኩል የማነ ከመገደሉ አስቀድሞ ለፌዴራል ወንጀል ምርመራ የተለያዩ ክሶች ሕወሓት ከተባረረ በኋላ ከትግራይ ክልል ይቀርቡበት እንደነበር ተሰምቷል።
ለፌደራል ፖሊስ ስለየማነ የደረሱ አቤቱታዎች እንደሚያስረዱት በተለያዩ ምክንያት መቀሌ የታሰሩ እስረኞችን አስፈታችኋለሁ በማለት ከእስረኞች እና ከእስረኛ ቤተሰብ ገንዘብ መቀበሉን እና በዚህም 3 ሰዎች መስከራቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጭ አክለውም የአንድ ግለሰብ መኪናን ሊብሬና መኪናዋን በመቀማት ውስጧ እንድትፈታ አስደርጎ ባለቤቱን በማስፈራራት የግለሰቡን ንብረት እንዲጠፋ ማድረጉን 2 የሚስክርነት ቃል መደመጡንም ነግረውናል። በተጨማሪም የጁንታውን አመራር መኖሪያ ቤት ራሱ ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በህገ ወጥ መንገድ የግል ጥቅም ፍለጋ በመበርበር ጭምር ከትግራይ ተወላጆች ክስ የቀረበበት ሲሆን በአጠቃላይ ግሰለቡ የግል ፍላጎቱን ለማሟላት ወደ ህገ ወጥ ተግባራት በመሠማራት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ለፖሊስ ከሚቀርቡበት አቤቱታዎች ለመረዳት እንደሚቻል ምንጩ ለዘ-ሐበሻ ተናገረዋል: