በአማራ እና በትግራይ ክልል አዋሳኝ ላይ በሚገኘው ተከዜ ግድብ አካባቢ ተደብቆ ሲደራጅ የከረመ ከ900 በላይ የሕወሓት ጦር ተደመሰሰ
ቀሪውን የሕወሓት ጁንታ እየተሹለከለከ ቦታ እየቀያየረ ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን አሁን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይህንን ቡደን በቁጥጥር ስር ለማዋል ወይንም ለመደምሰስ አዲስ የተጠና እና የተጠናከረ ኦፕሪሽን ከ2 ቀናት በፊት መጀመሩን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ።
በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በሚገኘው ተከዜ ግድብ አካባቢ የመሸገው የሕወሓት ኃይል የተከበበ ሲሆን በዚህ ዘመቻም ከ900 በላይ እንደገና እየተደራጀ እና ጥቃት ለማድረስ የሞከረ የሕወሓት መደምሰሱን ምንጩ አክለዋል።
የጁንታው አመራሮች አሉበት በተባለበት በዚህ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮቹ ሕወሓት 900 በላይ ወታደሮቹን ካጣ በኋላ በውጭ ሃገር በሚያሰራጫቸው ሚዲያዎች “የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች የተከዜን ግድብ ሊያፈርሱ ነው” የሚል ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ጀምሯል። የሕወሓት ደጋፊ ጋዜጠኞች ዜናውን በሰበር ሲያነቡት ሁሉ ድንጋጤ ይታይባቸው እንደነበር ሕዝብ የሚታዘበው ነው። ይህም ተከዜ ግድብ አካባቢ የተደበቀው የጁንታው አመራር ያለው አማራጭ ራሱን ለማዳን ይህን ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሕዝቡን ለማነሳሳትና በግርግር ለማምለጥ ነው የሚሉት የመከላከያው ምንጭ በዚህ አካባቢ የመሸገውን ኃይልን ለመምታትና ለመያዝ የሚደረገውን አዲሱን ኦፕሬሽን ለመምራት ከቀናት በፊት ጄነራል አበባው ታደሰ እና ጀነራል ባጫ ደበሌ ወደ ስፍራው ሄደው ከሌሎች የመከላከያው አመራሮች ጋር ትልቅ እቅድ ሲሰሩ እንደነበር ነግረውናል።
እስካሁን ያለው ኦፕሬሽን የተሳካ ነው። ከ900 በላይ የሕወሓት ጦር አባላትን ደምስሰናል ያሉት ምንጩ የተከበበው አመራር የተፈጸመበት ጥቃት እጅግ አስደንጋጭና የተጠናከረ ስለሆነበት ራሱን ለማዳን ሲል ሃሰተኛ መረጃዎችን እየፈበረከ የትግራይ ሕዝብ እና ብሔር ብሔረሰቦች እንዲያድነው በሚዲያዎቹ አማካኝነት እየተማጸነ ነው ይላሉ። ዛሬ ሕወሓቶች የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት የተከዜ ግድብን ለማፍረስ እየሄዱ ነው ሲሉ የሚያሰራጩት ሃሰተኛ መረጃን ከዚህ ቀደምም የትግራይ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልም ብሎት ነበር። ደብረጽዮን በመከላከያው ክፉኛ እየተቀጠቀጡ ባለበት ወቅትም መከላከያው ተከዜን እንደደበደበ እና እንዳፈረሰ ሃሰተኛ መረጃ አሰራጭቶ በኋላም ተጋልጦ እንደነበር አይዘነጋም።