በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የካናዳ ፓርላማ ውይይት ማድረጉ ተሰማ
የካናዳ ፓርላማ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ፣ በተለይም በእነ እስክንድር ነጋ የእስር ሁኔታ ላይ ምስክርነት መስማቱን ምንጮች ለሃበሻ ገለጹ።
በዚህ ውይይት ወቅት የፓርላማ አባላቱ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ አንዳሳሰባቸውም ተገልጿል።
በአሜሪካን እና ካናዳ ነዋሪ የሆኑ የባልደራስ ደጋፊዎች እና የህግ ባለሙያው ዶክተር ፍጹም አቻምየለህ ለፓርላማ አባላቱ እነ እስክንድር ነጋ ስለሚገኙበት ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ስጥተዋል።
በዚህም የስብአዊ መብት ኮሚቴ አባላቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመንገንዘብ የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስትን ላይ ግፊት እንዲያደርግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በተጨማሪም ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው ግጨት ውይይት እንደተካሄደ ምንጫችን ገልጿል።
ካናዳ በዓመት ወደ 200 ሚልዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በልማት እርዳታ ድጋፍ መልክ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ይታወቃል።