ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠራች፡፡
በኢትጵያና ኤርትራ ድንበር የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ዛሬ ሱዳን በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን መጥራቷን አስታውቃለች፡፡ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቀዋል አቀባይ መንሱር ቡላድ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (ኤኤፍፒ) በሰጡት መግለጫ ‹‹በአዲስ አበባ ካሉት አምባሳደራችን ጋር ስለኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት ለመመካከር ጠርተናቸዋል›› ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ መግለጫቸውን በመቀጠልም አምባሳደሩ ምክክሩን ከጨረሱ በኋላ ወደስራቸው እንደሚመለሱ ተናግረው የምክክሩን ባህርይ ለመግለፅ እንደተቆጠቡ ኤኤፍፒ ጨምሮ አስረድቷል፡፡ ባለፈው እሁድ ሱዳን በኢትዮጵያ ተወረርኩ የሚል መግለጫ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት እንዳስታወቀው ባለፉት ወራት የሱዳን ወታደሮች በርካታ የኢትዮጵያን መሬት ወረው ይገኛሉ፡፡