Archive

Category: News

ከሱዳን ሰርገው የገቡ ጥምር የህወሓትና ቅማንት ኃይሎች በሳራባ ካምፕ ታሰሩ | መከላከያው እና የአማራ ልዩ ኃይል ሽፍተውን ኃይል ከአይከል ጭልጋ መተማ መንገድ ጠራረጉ | አንድ ቀብሌ ብቻ ይቀራቸዋል

(ዘ-ሐበሻ) ከሕወሓት ጋር ተባብሮ በሱዳን ሰልጥኖ በሱዳን ኮሎኔሎች እየታዘዘ ጭልጋ ከተማ በመግባት በአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሃገር ለመጠብቅ ያስቀመጣቸው ወታደራዊ መገልገያዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው የቅማንት/ሕወሃት ሽፍታ ቡድንን የምጻዳቱ ተል ዕኮ እየተገባደደ መሆኑን አንድ የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገለጹ። ከመተማ እስከ ጭልጋ አይከል ድረስ ለቀናት ተዘግቶ በነበረው መንገድ የተነሳ …

የአማራ ክልል በየቦታው ተወጥሯል – ክልሉ የመንግስት ሥራ ሊያቆም ይችላል

የአማራ ክልል በየቦታው ተወጥሯል – ክልሉ በበጀት እጥረት የመንግስት ሥራ ሊያቆም ይችላል – በአዊ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በጭልጋ – በዋግ ህምራ ዞን በታጠቁ በሕወሓት የሚደገፉ ኃይሎች ጥቃት ተሰንዝሮበታል  (ዘ-ሐበሻ) የአማራ ክልል በበጀት እጥረት የተነሳ የመንግስት ሥራ ሊያቆም እንደሚችል እየተነገረ ባለበት በዚህ ሰዓት ክልሉን በሕወሓት የሚደገፉ ታጣቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለማፍረስ ወጥረውት ውጊያ…

በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ ማጀቴ፣ አላላ፣ አንጾኪያ እና አካባቢዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንዳለፉት 3 ቀናት የተኩስ ድምጽ ባይሰማም ታጣቂው ኃይል ራሱን ለሌላ ጥቃት እያዘጋጀ ሊሆን ስለሚችል ሕዝብ በጥንቃቄ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

–በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ ማጀቴ፣ አላላ፣ አንጾኪያ እና አካባቢዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንዳለፉት 3 ቀናት የተኩስ ድምጽ ባይሰማም ታጣቂው ኃይል ራሱን ለሌላ ጥቃት እያዘጋጀ ሊሆን ስለሚችል ሕዝብ በጥንቃቄ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ ” የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የገጠመንን ወረራና ጥቃት በተረጋጋና በተቀናጀ መንገድ…

ሽፍታው የሕወሓት የተራረፈ ቡድን ኮረም አካባቢ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ማስኮችን እና እህል የጫኑ መኪኖችን በእሳት አነደደ | ሹፌሮቹን ዘርፎ ረሽኗቸዋል

በተራ ሽፍታነት ተግባር ተሰማርቷል የሚባለው የተበታተነው የሕወሓት ኃይል ለትግራይ ሕዝብ እየሄደ የነበረን የኮቪድ 19 መከላከያ ማስኮችን፣ እና ሌሎች የ እርዳታ እህል የጫኑ መኪኖችን ኮረም አካባቢ ጨለማን ተገን አድርጎ በመዝረፍ እንዳቃጠላቸው ተገለጸ። የሽፍታው ቡድን ትግራይ እና ሕዝቡ ከተረጋጋ እኔ እረሳለሁ በሚል ምክንያት ሕዝቡ እርዳታ እንዳያገኝ፤ እርዳታ የጫኑ መኪኖችን መንገድ ላይ ጠብቆ…

ሸሽቶ እንደገና ተከዜ በርሃ የገባውን ትርፍራፊ የሕወሓት ኃይል ማሳደዱ ቀጥሏል | ዕድሜያቸው 16 እስከ 18 ያሉ ታጣቂዎች እጃቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰጡ

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ውጊያዎች ክፉኛ የተመታው ሕወሓት የተራረፈው ኃይል ሸሽቶ ተመልሶ ወደ ተከዜ በርሃ መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም መሰረት መከላከያው አሁንም የተራረፈውን የሕወሃት ኃይል ማሳደዱን ቀጥሏል። አንድ የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጭ እንደተናገሩት በዘመናዊ ጦር መሳሪያ በተጋዘ መልኩ ሌሊቱን የተራረፈው ኃይል የተሰባሰበት ተከዜ በረሃ በአየር ተደብድቧል። በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ…

ለአማራ ህዝብ መፈናቀልና መገደል ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ ሕገመንግስት እንዲቀየር በሚኒሶታ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተጠየቀ

የአማራ ህዝብ መገደልና መፈናቀል ይብቃ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በጠዋቱ በሚኒሶታ ስቴት ካፒቶል ደጃፍ በመውጣት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በስፍራው የሚትገኘው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንዳስታወቀችው በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች እየተሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለአማራ ህዝብ መገደል፣ መፈናቀል፣ መቁሰልና መገለል ምክንያት የሆነው ሕገመንግስት እንዲቀየር የሚጠይቀው ይገኝበታል። “ለሃገር ሰላ ሲባል ያሳየነው ት…

ጌታቸው ረዳ ለጠ/ሚኒስትሩ 1 ሳምንት ምላሽ ሰጠ

በርከት ያሉ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች በተለያዩ ሃገራት እየተሰጠ ስላለው የኮቭድ 19 ክትባቶች ባለሙያ አቅርበን መረጃ እንድናቀርብ ጠይቀዋል። በዚህ መሰረት በኒዮርክ ከ2017 እስከ ኮቪድ በዓለም ላይ እስከሚሰራጭበት 2020 ድረስ በህክምና ሙያ፤ እንዲሁም በላይቤሪያ ኢቦላ በተከሰተበት ወቅት ከ2001 እስከ 2014 መጨረሻ ያገለፈሉትን ዶ/ር አብይ ሙሉጌታን አበበን በኮቭድ ክትባት ዙሪያ ጠይቀናቸዋል። ዶ/ር አብይ የኮቪድ…

ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል። ብዙ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦችም መረጃውን እንድናጣራ ጠይቀውናል። ዘ-ሐበሻ ስለጌታቸው አሰፋ መገደል ከምንጮቹ እስካሁን ድረስ ለማረጋገጥ አልቻለም። በአማራ እና ትግራይ ክልል አቅጣጫ በሰቆጣ አቅጣጫ በርካታ የሕወሃት ሰዎች እንደተደመሰሱ መረጃው ዘ-ሀበሻ እጅ ያለ ሲሆን በጥቅሉ ጌታቸው ተገደለ የሚለውን…

8 ኮሎኔሎች እና አንድ ከፍተኛ የሕወሓት ጀነራል ቦራ አካባቢ ተደመሰሱ | ጄነራል ጻድቃን መሆኑ አልተረጋገጠም | ጀነራሉ በክብር የተቀበረ ይመስላል ተብሏል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተቆራረጠው የሕወሓት ኃይል ያለ የለለ ኃይሉን በማጠራቀም ከተከበበት ለመውጣት በሚያደርገው መፍጨርጨር ከፍተኛ ውድመት እየደረሰበት መሆኑን ዘ-ሐበሻ ከመከላከያ ምንጮች ማምሻውን ያረጋገጠው መረጃ አመለከተ። እንደመረጃው በአማራ እና ትግራይ ድንበር አካባቢ በማይጨው አቅራቢያ ቦራ፣ ጮቅሏ፣ ጨሌና፣ አላጄ፣ አሚላ፣ አምባላጌ፣ በተባሉት ከተሞች ትርፍራፊው የሕወሓት ኃይል ውጊያ ከፍቶ በመከላከያው እና በአማራ ልዩ ኃይል…

የባልደራስ የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባላት ማንነት ታወቀ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የአማካሪ ምክር ቤት አባላት ማንነት በይፋ ታወቀ። በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የሚገኙ እነዚህ ታዋቂ  ኢትዮጵያውያን  ፓርቲውን በተለያዩ እስትራቴጂክ እና ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በማማከር ድጋፍ መስጠታቸውንም ለዘሃበሻ የደረሱ መረጃዎች ጨምረው ገልፀዋል። አንጋፋውን ምሁር ፕሮፌስር ጌታቸው ሃይሌ ፣ዶክተር ሰማሃኝ ጋሹ፣ዶክተር አብርሃም አለሙ፣ አቶ ሃይለገብርኤል አያሌው፣የህግ ባለሙያው ዶክተር ፍፁም…