Archive

Category: News

ሊዝ ትሮሴል በኢትዮጵያ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አወጡ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ሊዝ ትሮሴል በኢትዮጵያ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገን በማድረግ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳርና ሌሎችም አካባቢዎች መጠነ ሰፊ እስርና ፍተሻ እየተከናወነ መሆኑ ድርጅታቸውን እንዳሳሰበው ገልፀዋል፡፡ ይህ ከሚከናወንባቸው ውስጥ…

በአዲሱ መጠሪያው ሜታ የተባለው ፌስ ቡክ ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎቹ አዲስ መመሪያ አውጥቷል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲሱ መጠሪያው ሜታ የተባለው ፌስ ቡክ ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎቹ አዲስ መመሪያ አውጥቷል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ የግጭት ስጋት ያለባት አገር እንደመሆኗ መጠን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው አገራት ተርታ አስቀምጠናት ቆይተናል›› ሲል የጀመረው መመሪያው ባለፉት ሁለት አመታትም በኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻንና ለግጭት የሚያነሳሱ ይዘቶችን ለመቀነስ ከፍተኛ ወጪ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አሁን ደግሞ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱ…

የአሜሪካ ስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) አስገራሚ ትንበያ በኢትዮጵያ ላይ አወጣ

(የዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ከሚገኝ መረጃ በየጊዜው የሚወጣው ‹‹ኢንሴኪዩሪቲ ኢንሳይት›› ዛሬ ኢትዮጵያን የተመለከተ ትንታኔና ትንበያውን አቅርቧል፡፡ ትንታኔውን የጀመረው በአዲሱ የተቃዋሚዎች ጥምረት ወደፊት መግፋት የኢትዮጵያ መንግስት ጫና ውስጥ መግባቱን በመግለፅ ሲሆን በህወሀትና በኦነግ ሸኔ እየተደረገ ያለው ውጊያ አላማው በፍጥነት ሁሉንም ወደአዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶች መዝጋት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህም መንግስት…

ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያን ጉሮሮ በቀናት ውስጥ እዘጋለሁ በሚል የኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሆነውን ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ። በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ወደ ሚሌ በባቲ መስመር እንዲሁም በጭፍራ በኩል በ2 አቅጣጫ ቆርጦ ለመሄድ ያለ የሌለ ሃይሉን ለወራት ገብሯል። ለደጋፊዎቹም ትናንት…

1 ቢሊዮን ብር የሚያወጣውን የብሔራዊ ቤተመንግስት ዕድሳት ፕሮጀክት ለማስጀመር የኮንትራክተሮች ምርጫ ከጫፍ ደረሰ

(ዘ-ሐበሻ ዜና)አንድ ቢሊዮን ብር የሚያወጣውን የብሄራዊ ቤተ መንግስት እድሳት ፕሮጀክት ለማስጀመር የኮንትራክተሮች ምርጫ ከጫፍ እየደረሰ መሆኑን ዘ ሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ ዛሬ ዘግቧል፡፡ በሀይለስላሴ የተሰራውን ይህንን ቤተመንግስት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እቅድ መቀረፁ ይታወቃል፡፡ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኒኤል ማክሮን የዛሬ ሁለት አመት ተኩል ገደማ ቤተመንግስቱን በጎበኙበት ወቅት ይህንን እቅድ በፋይናንስ ለመደገፍ ቃል መግባታቸውም…

የኬኒያው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ላይ እነዚህን ነገሮች ሲያደርጉ ከርመው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በባይደን አስተዳደር ወደኋይት ሀውስ የተጠሩ መጀመሪያው የአፍሪካ ፕሬዝደንት መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎ ሰሞኑን የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት በኬንያ መመላለስ ማብዛታቸው የሚታወቅ ሲሆን በመጪው ሰኞ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም ናይሮቢ ይገባሉ፡፡ አሜሪካ ከኬንያ ጋር እንዲህ አይነት የቅርብ ትስስር የፈጠረችው ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የአደባባይ…

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደነበር በመጥቀስ ተቃውሞውን ጀምሯል። ስለዚህም የአሜሪካ መንግስትም የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቆ ምክንያቶችን ዘርዝሯል። 1. “ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት…

የዘ-ሐበሻ የዕለቱ 9 አጫጭር ዜናዎች

1. የዋግ ህምራ ሰቆጣ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አቡነ በርናባስ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተሰማ፡፡ አደባባይ ሚዲያ እንዳስታወቀው ብፁእነታቸው ታፍነው ስለመወሰዳቸው ቢነገርም ምንም ችግር እንዳላጋጠማቸው ከምንጮቹ ሰምቷል፡፡ በአካል ጳጳሱን ያገኙ ሰዎችን ምስክርነት ማግኘቱንም አስረድቷል፡፡ ብፁእነታቸው የድጓ፣ የቅኔ፣ የዝማሬ መዋስት፣ የሀዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን ሊቅና የትህትና መምህር እንዲሁም የፀሎት አባት መሆናቸውንም…

በዳውንት ወደ በታች ጋይንት ቆርጦ ሊመጣ የነበረው የሕወሓት ኃይል ተመታ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) አሸባሪው እና ወራሪው የሕወሓት ኃይል በጋሸና መስመር ያለውን የኢትዮጵያን ኃይሎች አሰላለፍ ለማዛባት በዳውንት በኩል ቆርጦ ወደ ታች ጋይንት ለመግባት ሙከራ እያደረገ መሆኑን ከቀናት በፊት በዘ-ሐበሻ ዜና ዘግበን ነበር። ዛሬ የደቡብ ጎንደር የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ይህን አረጋግጠው ከሰሞኑ በዳውንት መስመር አድርጎ በታች…