Archive

Category: News

በኦሮሚያ ክልል በገብረ ጉራቻ እና ፍቸ መሃከል ዛሬም የታጠቁ ሃይሎች አሽከርካሪወች ላይ ተኩስ ከፍተዋል መኪና አቃጥለዋል

በኦሮሚያ ክልል ፊቼ እና ደብረጉራቻ አካባቢ ባለችው አሊደሮ ከተማ ታጣቂዎች በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በሰላማዊ ሹፌሮች ላይ ጥቃት ሰነዘሩ። ይህን ተከትሎ በኦሮምያ ክልል አሊደሮ በተባለው አካባቢ በደረሰው የመኪና መቃጠልና በሰዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ምክንያት ከአማራ ክልል ወደ አ/አበባ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መዋሉ ተገልጿል። ትንናት ግንቦት በ14/09/13 ሌሊት ላይ…

ከአንድ ወር በፊት በጌታቸው ረዳ መንገድ መሪነት የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል አበርጌሌ ያደረሱት ውድመት ይፋ ሆነ

(ዘ-ሐበሻ) ከአንድ ወር በፊት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ሚያዝያ 17 ቀን ለ18 /2013 ንጋት 11: 00 ሰዓት አካባቢ የጁንታው ርዝራዥ የአበርገሌ ወረዳ ማእከል በሆነችዉ ኒየረ-አቁ ከተማ ሰርጎ በገባበት ወቅት ከቀጠፈብን ህይወት በተጨማሪ በቁሳዊ ሃብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ይፋ ሆነ። የአበርገሌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ…

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ሊጥል ነው ተባለ

(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ያቀረበው የኢትዮጵያ መንግስት አልቀበልም ብሏል በሚል ማዕቀብ ሊጥል መሆኑን የዘ-ሐበሻ የዲፕሎማቲክ ምንጮች አስታወቁ። የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ላይ የሚጣለውን ማዕቀብ የአሜሪካ መንግስት ከአሁን ሰዓት በኋላ በማንኛውም ሰዓት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የአሜሪካ መንግስት…

በትናንትናው ዕለት ደግሞ 130 የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች በሁመራ በኩል ሊገቡ ሲሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ልዩ ኃይል ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ የመከላከያው ምንጭ አስታወቁ

(ዘ-ሐበሻ) በሱዳን ካርቱም አና ገዳሪፍ የሚገኙ የትግራይ ኮሚኒቲ አመራሮች ህሓትን ለማጠናከርና ሃገር ቤት ያለውን አመራር ለማስወጣት በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና የተለያዩ አረብ ሀገራት የሚገኙ የህወሓት ደጋፊዎች ያሰባሰበውን ገንዘብ መድሃኒት በመግዛት ወደ ፖርት ሱዳን ካስገባ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ከሳምንት በፊት ሞክረው 320 የሚሆኑ በሱዳን የሰለጠኑት የጁንታው ታጣቂዎች መደምሰሳቸውንና የተወሰኑትም መማረካቸውን መከላከያው…

ሱዳን ሰልጥነው የተላኩ 500 የሚሆኑ የጉሙዝ ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ተደመሰሱ

(ዘ-ሐበሻ) “በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ አንደኛ ጠላት ሱዳን ነች። ድንበራችንን ዘልቆ በመግባት መሬት መቆጣጠሩና ንጹሃንን እየገደለ መዝረፉ ሳያንስ፤ በአንድ በኩል የሕወሓትና ቅማንት ታጣቂዎችን፣ በሌላ በኩል የጉሙዝ ታጣቂዎችን አሰልጥና፣ ከለላ ሰጥታ እየላከች ኢትዮጵያን ሰላሟን ለመንሳት ተግታ እየሰራች ነው” ይላሉ የዘ-ሐበሻው የመከላከያ ምንጭ መረጃ ማቀበሉን ሲጀምሩ። “የኢትዮጵያ መንግስት ስጋቱ የሆነውን የሱዳን መንግስት ከአንድ…

በኦርቶዶክስ ቤ/ክ የመቀሌ ሃገረ ስብከት የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ ሕዝብን ክዷል የሚል አደገኛ መግለጫ አወጣ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር “የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግራይ ህዝብንና ቤተክርስትያን ከድተዋል” የሚል አደገኛና ከፋፋይ ይዘት ያለው መግለጫ ዛሬ ማውጣቱታቸው ቁጣን ቀስቀሰ። የትግራይ ሲኖዶስን እናቋቁማለን በሚል እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙት አካላት ጋር እየሰሩ የሚገኙት የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር ዛሬ ያወጡት መግለጫ ቤተክርስቲያንን በመከፋፈል…

“በዚህ ቁመና ላይ ሆነን ፣ ጁንታው ነገ እንገባለን…የአስር ብር ርቀት ላይ ነን…ደግሳችሁ ጠብቁን የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም ህዝቡ አይደናገርም ” – ሜ/ጀ ክንዱ ገዙ

ራሱን የሕወሓት የሽፍታ ቡድን ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ገብረገብረ ጻድቃን በድምጺ ወያኔ ላይ በድምጽ ከጠፋ ቆይቷል። ሆኖም ግን ድምጺ ወያኔ ገበረገብረጻድቃን የድል ዜና ነገሩኝ እያለ በሰበር ዜና መናገሩን ቀጥሏል። ዛሬም የገብረገብረጻድቃን ድምጽ በሌለበት ዘገባው የተለያዩ የድል ዜናዎችን ለደጋፊዎቹ አሰምተዋል። ሚያዝያ 15 እና ሚዚያ 16 በዕዳጋ አርጊ ነበለት፤ በዓዴት፣ በአግበ’ጅጅቀ፣ በተንቤን…

ከሱዳን ሰርገው የገቡ ጥምር የህወሓትና ቅማንት ኃይሎች በሳራባ ካምፕ ታሰሩ | መከላከያው እና የአማራ ልዩ ኃይል ሽፍተውን ኃይል ከአይከል ጭልጋ መተማ መንገድ ጠራረጉ | አንድ ቀብሌ ብቻ ይቀራቸዋል

(ዘ-ሐበሻ) ከሕወሓት ጋር ተባብሮ በሱዳን ሰልጥኖ በሱዳን ኮሎኔሎች እየታዘዘ ጭልጋ ከተማ በመግባት በአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሃገር ለመጠብቅ ያስቀመጣቸው ወታደራዊ መገልገያዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው የቅማንት/ሕወሃት ሽፍታ ቡድንን የምጻዳቱ ተል ዕኮ እየተገባደደ መሆኑን አንድ የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገለጹ። ከመተማ እስከ ጭልጋ አይከል ድረስ ለቀናት ተዘግቶ በነበረው መንገድ የተነሳ …

የአማራ ክልል በየቦታው ተወጥሯል – ክልሉ የመንግስት ሥራ ሊያቆም ይችላል

የአማራ ክልል በየቦታው ተወጥሯል – ክልሉ በበጀት እጥረት የመንግስት ሥራ ሊያቆም ይችላል – በአዊ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በጭልጋ – በዋግ ህምራ ዞን በታጠቁ በሕወሓት የሚደገፉ ኃይሎች ጥቃት ተሰንዝሮበታል  (ዘ-ሐበሻ) የአማራ ክልል በበጀት እጥረት የተነሳ የመንግስት ሥራ ሊያቆም እንደሚችል እየተነገረ ባለበት በዚህ ሰዓት ክልሉን በሕወሓት የሚደገፉ ታጣቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለማፍረስ ወጥረውት ውጊያ…

በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ ማጀቴ፣ አላላ፣ አንጾኪያ እና አካባቢዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንዳለፉት 3 ቀናት የተኩስ ድምጽ ባይሰማም ታጣቂው ኃይል ራሱን ለሌላ ጥቃት እያዘጋጀ ሊሆን ስለሚችል ሕዝብ በጥንቃቄ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

–በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ ማጀቴ፣ አላላ፣ አንጾኪያ እና አካባቢዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንዳለፉት 3 ቀናት የተኩስ ድምጽ ባይሰማም ታጣቂው ኃይል ራሱን ለሌላ ጥቃት እያዘጋጀ ሊሆን ስለሚችል ሕዝብ በጥንቃቄ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ ” የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የገጠመንን ወረራና ጥቃት በተረጋጋና በተቀናጀ መንገድ…