Archive

Author: Editor

የፊታችን ሰኞ የሙስና ክስ ሊመሰረትበት ክስ የተጠናቀቀበትን የሕወሓት ባለሃብት ሙሉጌታ ፒፓን ክሱን አሰርዞ በዋስ ለማስፈታት እየተሰራ ነው ተባለ

ከአሜሪካ ቦስተን ከተማ ፓርኪንግ ሰራተኛነት ተነስቶ በፍጥነት የነስብሃት ነጋን ገንዘብ በማንቀሳቀስ እጅግ ሲበዛ ሚሊየነር እንደሆነ የሚነገርለት ባለሃብቱ ሙሉጌታ ፒፓን ከእስር ለማስለቀቅ በመንግስት ውስጥ ያለ ህቡዕ መዋቅር እየሰራ መሆኑ ተጋለጠ። ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት የሕወሓት ዋና የገንዘብ ምንጭ ባለሃብቱ ሙለር ፒፓ (ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ) የፊታችን ሰኞ የሙስና ክስ ሊመሰረትበት በዝግጅት ላይ ነበር።  ማስረጃዎች…

በቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራው የሕወሓት ጁንታ የዲፕሎማሲ ቡድን በየቀኑ ሃሰተኛ መረጃዎችን በትዊተር እያሰራጨ

በቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራው የሕወሓት ጁንታ የዲፕሎማሲ ቡድን በየቀኑ ሃሰተኛ መረጃዎችን በትዊተር እያሰራጨ የዓለም ታላላቅ ተቋማትን እና ሃገራትን እያሳሳተ እንደሆነ እና ይህም የኢትዮጵያን መንግስት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለው እንደሚገኝ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ምስጢራዊውን መረጃ ለዘ-ሐበሻ ተናገሩ::  ትናንት ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ከጀርመኗ መሪ አንጌላ ማርኬል ጋር ከተወያዩ በኋላ ወዲያውኑ በውጭ ላለው ዲያስፖራ “ዳሩ…

ዋልድባ ገዳም አካባቢ የጀነራል ታደሰ ወረደ ጦር በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ ከፍቶ ውጊያ ገጥሟል

እየተካሄደ ባለው የሕወሃት አመራሮችን እና የጦር መኮንኖችን በቁጥጥር ሥር የማዋል ወይም የመደምሰስ ትግል የመጨረሻው ም ዕራፍ ላይ ይገኛል:: ጀነራል ታደሰ ወረደ, ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ እና ሌሎችም የሚገኙበት ይህ የሕወሓት 200 የሚሞላ ጦር በዋልድባ ገዳም አካባቢ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጅ እንዲሰጡ በማይክራፎን በተደረገ ጥሪ ቢጠየቁም አሻፈረኝ በማለት ውጊያ መክፈቱን የዘ-ሐበሻ ምንጭ…

ኮ/ል ልኡል ገብረዋህድ ብርሃኔ ከደቡብ ሱዳን ተላልፎ ተሰጥቶ በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ተረጋገጠ

(ዘ-ሐበሻ) በፌደራል ፖሊስ ከሚፈለጉት የሀገር መከለከያ ሚኒስቴር ሰብአዊ መረጃ ሃላፊ) ብ/ጄ መብራህቱ ወ/አረጋይ ፣ ኮ/ል ከበደ ገብረሚካኤል ፣ ኮ/ል ነጋሲ ስዩም በመሆን በሰሜን እዝ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ አመራሮችን ሲያሰልል እና ፕሮፋይላቸውን ለክልሉ የደህንነት ክንፍ ሲያቀብል የነበረው ኮ/ል ልዑል ገብረዋህድ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ ተሰጥቶ በአሁኑ ወቅት በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ…

የሆራ አዲስ አበባ የኢሬቻ ክብረበዓል በሰላም ተጠናቀቀ

ዛሬ በአዲስ አበባ የተከበረው የሆራ አዲስ አበባ የኢሬቻ ክብረበዓል የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት በወሰነው መሠረት በውስን የተሳታፊ ቁጥር ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል::

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ያስታወቁ ሲሆን ይህን ተከትሎ የትዊተር ገፃቸው በአማርኛ መልእክቶች ተጨናንቋል

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ያስታወቁ ሲሆን ይህን ተከትሎ የትዊተር ገፃቸው በአማርኛ መልእክቶች ተጨናንቋል፡፡  ይህም በዛሬው እለት በአለማችን መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ውሏል፡፡ እነዚህ የአማርኛ መልእክቶች አብዛኛዎቹ አስፈሪና የሰይጣን የሚባል ምስሎችን የያዙ መሆናቸውን ማሽቢል የተሰኘው ድረ ገፅ ዘግቦታል፡፡ ይህ ድረ ገፅ እንዳንዶቹን መልእክቶችንም አቅርቧል፡፡ ጊዮ የተባሉ ሰው…

“እውነት ከአንባገነኖች ክንድ ትበረታለች”! – የባልደራስ መግለጫ

“እውነት ከአንባገነኖች ክንድ ትበረታለች”!  የባልደራስ መግለጫ ብሄራዊ መግባባት ሽብር ባልፈጸመ ሰላማዊ ታጋይ ላይ የሽብር ክስ በመመስረት ህጉን የፖለቲካ ተገዥ በማድረግ አይገኝም!!!እናት አገራችን ውዲቷ ኢትዮጵያ ከአያት ቅድም አያቶች አጥንት ፍላጭ ተማግራ፣ አፈሯ በደማቸው  ተለዉሶ ተቦክቶና ተጋግሮ ለሺዎች ዘመን የቆመች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ ነገዶች ባህል ከባህል፣ሃይማኖት ከሃይማኖት ነገድ ከነገድ ተስበጣጥሮ ያቆማት…

የአንድ የኢትዮጵያ ሲኒ ቡና ዋጋ 50 ፓውንድ (ከሁለት ሺህ ብር በላይ)

የለንደን አንድ ቡና መሸጫ መደብር በዩናይትድ ኪንግደም እጅግ ውድ የሆነውን አንድ ሲኒ ቡና መሸጥ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የዚህ አንድ ሲኒ ቡና ዋጋ 50 ፓውንድ(ከሁለት ሺህ ብር በላይ) ሲሆን ለገበያ የቀረበውም 15 ሲኒ ቡና ብቻ ነው፡፡ ይህ ቡና ቤት ኩዊንስ ኦፍ ሜይፌር የሚባል ሲሆን ይህንን ውድ ቡና አፍልቶ እየሸጠ ያለው ከኢትዮጵያ በጨረታ…

ይድረስ ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት – ከኮሎራዶ የአማራ ማህበር የተላከ

መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. (September 18, 2020) ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ – የአማራ ክልል ፕሬዚደንት:- በአማራ ክልል ለምትገኙ የትላንቱ ብአዴን/አዴፖ የዛሬው ብልፅግና ፖርቲ የመንግስት አመራር አካላት በሙሉ (PDF) ይህንን ደብዳቤ ስንፅፍላችሁ በአሁኑ ጊዜ በአማራ ህዝባችን ላይ የሚደረገውን በአለም ውስጥ ከፍተኛ ሰቆቃ የሞላበት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየተመለከታችሁ ወይም ከተባባሪነት ያላነሰ ተሳትፎ…

በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት መሰረተ ልማትና የአይቲ ስልጠና በደቡብ ኮሪያው ሲማኡል ንቅናቄ ልምድ እንዲወሰድበት አደርጋለሁ›› – ዶ/ር መኩሪያ

‹‹አንድ ኢትዮጵያዊ ሚኒስትር ከኮሪያ አድቫንስድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት በዶክትሬት ዲግሪ ተመረቁ›› ሲል ጎንጋ ዶት ኮም ዛሬ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው የተመረቁት አቶ መኩሪያ ሀይሌ ተክለማሪያም ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው፡፡ ዶክትሬታቸውን ያገኙት በግሎባል ኢንፎርሜሽን ኤንድ ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፕሮግራም ሲሆን ትምህርቱንም ላለፉት አራት አመታት ሲከታተሉ ቆይተው ባለፈው ወር…