በሰሜን ጎንደር ማይጠምሪ ግንባር እና በጋሸና መስመር እየተቀጠቀጠ ያለው የሕወሓት ኃይል በደቡብ ወሎ በኩል ግን ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ሕዝብ ከከተማዎች እንዲሸሽ በማድረግ ለመስፋፋት ቢሞክርም፤ በሕዝብ እና በኢትዮጵያ ኃይሎች ብርታት ኢላማው እንዲሰናከል ተደርጓል።
የሕወሓት ቡድን ወደ አፋር ጭፍራ ተራሮች ላይ በመሆን መድፍና ከባድ መስሪያዎችን በመተኮስ ንጹሃንን በመግደል ወደ ጭፍራ ለመግባት ያደረገው ጥረት በአፋር ልዩ ኃይል እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቢከሽፍበትም፤ ይህ ኃይል ወደ ወረባቦ ተቆርጦ ቢመጣም የኢትዮጵያ ኃይሎች ደም ሰሰውታል። በዚህ አካባቢ ሕወሓት አንድ ብርጌድ የሚሆን ሰራዊት ይዞ የመጣ ቢሆንም ይህ ሁሉ ኃይል በኢትዮጵያ ሃይሎች መደምሰሱን እና የተቀረው መበታተኑን የመከላከያው ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
በውርጌሳ አካባቢ አሸባሪውና አረመኔው የሕወሓት ኃይል 28 ወጣቶችን በመያዝ አማራ በመሆናቸው ብቻ በአንድ ቤት ውስጥ በማስገባት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት እንደለኮሰባቸውና እንዳቃጠላቸው ከስፍራው የመጡ መረጃዎች አመልክተዋል። በዚህ አካባቢ የገባውን የጁንታውን ኃይል በአስቸኳይ እርምጃ ወስዶ የልጆቹን ደም መበቀል ያስፈልጋል የሚሉት ምንጩ በሌሎችም አካባቢዎች እንዲሁ ወጣቶችን ሲገድል የቆየው ይህ አረመኔ ቡድን በውርጌሳ የፈጸመው ግን ከአረመኔም አረመኔ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ሕዝብ በአስቸኳይ ተነስቶም ይህን ኃይል ሊያጠፋው ይገባልም ብለዋል።
በተጨማሪም ወደ ወገልጤና ደላንታ ለመግባት የሞከረው ይኸው የሕወሃት ኃይል ጉሽ ሜዳ ላይ በኢትዮጵያ ኃይሎች ተመቶ ሙትና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን የተቀረው የሕወሓት ኃይልም ሬሳውን እያንጠባጠበ ወደ ኋላ ሸሽቷል። 42 መሳሪያ የጫኑ ኦራል እና ሲኖ ከነ ሰራዊቱ አፈር ከድሜ ተቀላቅሏል።
ሆኖም ወደ ኋላ የሸሸውና አስከሬኑን እያንጠባጠበ የሄደው ኃይል እንደገና ሊደራጅ ስለሚችል ደጋግሞ እግር በእግር እየተከተሉ ማውደም እንደሚገባ ተነገሯል።
በተጫማሪም ይኸው የሕወሓት ኃይል ወደ ሐይቅ ለመሄድ በጠዋት ጉዞ ጀምሮ እንደነበር የተናገሩት የእመከላከያው ምንጭ ሐይቅ ሳይደርስ ድንገት የኢትዮጵያ አየር ወለዶች በመምጣት ይህንን የሕወሓት ዘራፊ እና አስገድዶ ደፋሪ ወራሪ ኃይል ወደ አፈርነት ቀላቅለውታል። ሐይቅን የመቆጣጠር ሕልሙንም አሰናክለው የተራረፈው ኃይል አስከሬኑን ሳይለቅም እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈርጥጧል።
ውጫሌ ተራራዎች ላይ ሆኖ ወደ ሕዝብ ሲተኩስ የነበውና ሕዝብን ሲረብሽ የነበረው የሕወሓት ኃይልም በኢትዮጵያ ኃይሎች ይህ ዜና እየተጠናከረበት ባለበት ሰዓት እየተወቀጠ ነው። ኢትዮጵያውያን ሕወሓት ከሚያሰራጨው የሴራ የፖለቲካ ትንትና፤ የተከዳህ ትርክት ራሳቸውን አርቀው ለመከለካያው ደጀን እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ኃይሎች ዛሬ ጁንታውን በረፈረፉባቸው የውጊያ ሜዳዎች የአካባቢው ማህበረሰብ የሚችለው እየተዋጋ የማይችለው ደጀን በመሆን ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ እንደሚገኝም መረጃው ለዘ-ሐበሻ ደርሷል።
—