Site icon www.zehabeshanews.com

በአዳማ አንድ የምርጫ ጣቢያ ተበጠበጠ

 

ለ6ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምርጫ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል እንደቀጥለ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ችግር ማጋጠሙ አልቀረም። ከነዚህ መካከል በአዳማ ከተማ ጉርሙ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ አባጓሮ ተፈጥሮ ወዲያው ተረጋግቷል።
አምባጓሮውን የፈጠሩት እንደማንኛውም መራጭ ሰልፋቸውን ጠብቀው ድምጽ የሚሰጥበት ጣቢያ ውስጥ የገቡ ወጣቶች መሆናቸውን የሚናገሩት የአይን እማኞች ወጣቶቹ የምርጫ ኮሮጆውን ጨምሮ ሌሎችንም ወረቀቶች በመበታተን ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረው ነበር። ወጣቶቹ ‹‹እነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ የሌሉበትን ምርጫ አንፈልግም›› ሲሉ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።
ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከሩት ወጣቶቹ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርጫ ጣቢያውም መራጮችን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በሰላም ምርጫውን ማካሄድ መቀጠሉ ተሰምቷል።

Exit mobile version