Site icon www.zehabeshanews.com

የሕወሓት ታጣቂዎች ዱቂት ሰርቀው ሄዱ

Getachew Reda

(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ድህር ግባ ቀበሌበቁጥር 34 የሚደርሱ የአሽባሪዉ ሕወሓት ቡድን አባላት ለ3ኛ ጊዜ እንደለመዱት አድፍጠዉ በመግባት ህዝብ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲሞክሩ በአራት የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ህዝቡን ባለማስደፈር ከታጣቂዉ አሽባሪ ቡድን ጋር በጀግንነት በመፋለምና አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደ ነበረበት እንደተመለሰ የተቀረውም መደምሰሱን የወረዳው ኮምዩኒኬሽን ማስታወቁን መዘገባችን ይታወቃል።

ዛሬ ዘ-ሐበሻ ከምንጮች ባገኘው ተጨማሪ መረጃ መሰረት ለሁለት ሰዓታት ታጣቂዎቹ እየተፋለሙ ባሉባት ሰዓት የተወሰኑ ታጣቂዎች ወደ ከተማው ትምህርት ቤት በመግባት ለህጻናት የተዘጋጀ ምግብና ዱቄት ጭምር ዘርፈው ሄደዋል።

ይህ ከውጭ ሃገር መንግስታት የተገኝውና ለተማሪዎች ምግባ የሚውለውን ምግብ መጋዘን የሕወሓት ታጣቂዎች በመስበር እህል ጭነው በመሄዳቸው ትምህርት መቋረጡንም ነው የዘ-ሐበሻ ምንጭ የገለጹት። ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜያት ያህል ወደ አማራ ክልል አበርጌሌ በመግባት ጥቃት የሰነዘረው የሕወሓት ታጣቂ አሁን ለ3ኛ ጊዜ ለተማሪዎች ምግብ የተዘጋጀ ምግብ ዘርፎ በመሄዱም የአካባቢውባለስልጣናት ለእርዳታ ድርጅቶችና የክልሉ መንግስት ማመልከቻ በማስገባት በቶሎ ምግቡ እንዲተካላቸውና ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል እየተሰራም ነው ተብሏል።

ለ3ኛ ጊዜ የመጡት ታጣቂዎች የተወሰኑት ምግብ ሰርቀው ቢሄዱም የተቀሩት የሕወሓት ታጣቂውች ከነዘረፉት ዱቄት በሚኒሻዎቹ የቀበሮ ጉድጓድ እንዲገባ ቢደረግም አሁንም ይህ የትግራይ እና የአማራ ክልልን የሚያዋስነውና ለጥበቃ አመቺ ባልሆነው ቦታ ተመሳሳይ ጥቃት እያዘናጉ ሊፈጽሙ ስለሚችሉ ሌላዉ ቀበሌም የ እነዚህን 4 ሚሊሻዎች ተሞክሮ በመዉሰድ አካባቢዉንና ህዝቡን ከዚህ ከተበታተነ አሽባሪና ሽፍታ ቡድን ተደራጅቶ ሊጠብቅ ይገባል ሲል የአበርጌሌ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ጥሪውን አቅርቧል።

ይህ በ እንዲሀ እንዳለ ኢንተርኔት አጥቶ የሰነበተው ጌታቸው ረዳ ከተደበቀበት የአማራ እና ትግራይ ድንበር አካባቢ በአሜሪካ ማዕቀብ ዙሪያ ተናግሯል። ጌታቸው ከመንግስት ጋር “”ድርድሩም ተደረገ፣ የአሜሪካ መንግስት አቅምም አረገ አላረገ፣ ዋናው አቅም የትግራይ ህዝብ አቅም ነው። እነዚህ ሰዎች ፈልገውም ባይሆን ተገደው ከትግራይ ይወጣሉ።” በማለት ኢትዮጵያን እያንቋሸሸ ሲናገር ተደምጧል።

Exit mobile version