በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ መጣሉን በይፋ መነገሩን ተከትሎ መነጋገሪያ ሆኗል። በርካታ ኢትዮጵያውያንም ከህግ አንጻር ይህ ጉዳይ እንዴት እንደኢታይ ጥያቄ አላቸው። የቪዛ ክለላ ምንድን ነው? አሜሪካ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዝና ያደረገችው ነው ማለት ይቻላል ወይ? ቀጥሎ የሚወሰው እርምጃ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ምላሽ ምን መሆን አለበት? አሜሪካ የኢኮኖሚው ማዕቀቡንም ኮንሲደር እናደርጋለን እያለች ነው ይህ ምን ማለት ነው? የአሜሪካ ውሳኔ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ቦታ አያሳጣውም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ይህንን ተከትሎ ዘ-ሐበሻ በአሜሪካ ቦስተን የሚገኘውን ታዋቂውን ጠበቃ ደረጀ ደምሴ ቡልቶን ለማብራሪያ ግብዟል። እንዳያመልጣችሁ ተመልከቱት።