Site icon www.zehabeshanews.com

አሜሪካ ማዕቀቡን ይፋ አደረገች – ከአሜሪካ ማዕቀብ በስተጀርባ ያሉ ምስጢሮች

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የቪዛ እቀባ የአማራ ክልልና የሕወሓት ባለሥልጣናትን ጨምሮ በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ መጣሉን ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በኩል ይፋ አድርጓል። ይህ ማዕቀብ እንደሚጣል ዘ-ሐበሻ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ከአራት ቀን በፊት በሰበር ዜና መዘገቡ አይዘነጋም።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አሁን አሁን ማምሻውን ባወጡት መግለጫ በትግራይ ጦርነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ተሳትፎ ያላቸው የቀድሞና የአሁን ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እቀባ መጣሉን ተናግረዋል። በቪዛ እቀባው የአማራ ክልል ባለሥልጣናት፣ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት፤ በልዩ ኃይል መሪዎች እንዲሁም በሰብዓዊ ቀውሱ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ሁሉ ተካቷል። በአሜሪካ ሕግ የቪዛ ክልከላ የተደረገባቸው ሰዎች ስም በይፋ ስለማይገለጽ ብሊንከንም ይህን አልጠቀሱም። ይህንን ተከትሎ የዘ-ሐበሻው ጋዜጠኛ
ክንፉ አሰፋ “ከአሜሪካ እቀባ በስተጀርባ ያሉ ምስጢሮች” ሲል አንድ ሊያመልጥዎ የማይገባ ጽሁፍ አቅርቧል እንደሚከተለው አነብላችኋለሁ አብረን እንቆይ።


ጸሐፊ፡ ክንፉ አሰፋ
አቅራቢ፡ ሔኖክ ዓለማየሁ

Exit mobile version