(ዘ-ሐበሻ) በሱዳን ካርቱም አና ገዳሪፍ የሚገኙ የትግራይ ኮሚኒቲ አመራሮች ህሓትን ለማጠናከርና ሃገር ቤት ያለውን አመራር ለማስወጣት በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና የተለያዩ አረብ ሀገራት የሚገኙ የህወሓት ደጋፊዎች ያሰባሰበውን ገንዘብ መድሃኒት በመግዛት ወደ ፖርት ሱዳን ካስገባ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ከሳምንት በፊት ሞክረው 320 የሚሆኑ በሱዳን የሰለጠኑት የጁንታው ታጣቂዎች መደምሰሳቸውንና የተወሰኑትም መማረካቸውን መከላከያው ባለፈው ሳምንት መዘገቡ ይታወቃል።
በትናንትናው ዕለት ደግሞ 130 የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች በሁመራ በኩል ሊገቡ ሲሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ልዩ ኃይል ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ የመከላከያው ምንጭ አስታወቁ።
ዘ-ሐበሻ ከሁለት ወር በፊት ሕወሓት በቀድሞው የትግራይ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ተኪኡ መአሾ እና በከዱ የጦር ኃይል አባላት የሚሰለኑ 820 አካባቢ ጦር በሱዳን እያዘጋጀ መሆኑንና ሌሎ ምልመላዎችንም ከስደተኛ ካምፖች እያደረገ መሆኑን ይህም በሱዳን መከላከያና በሱዳን ደህንነት መስሪያ ቤት እንደሚደገፍ መዘገቡ ይታወሳል።
ከነዚህ ኃይሎች መካከል 320ው ባለፈው ሳምንት መጨረሻቸው የለየ ሲሆን ትናንት ደግሞ መድሃኒት ጭነው እየገቡ የነበሩ 130 የሚሆኑ የሕወሓት ኃይሎች ከነያዙት መድሃኒት መንገድ ቀርተዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጭ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና አረብ ሃገራት ለሕወሓት ይህን መድሃኒት የሚልኩም ከስረዋል፤ ይልቁንም እርዳታ የሚያስፈልገውን የትግራይ ሕዝብ ቢረዱ ይሻላቸዋል ብለዋል።
ከውጭ የሚላከውን ገንዘብና መድሃኒት ለህወሓት አመራሮች በማድረስ ላይ የሚገኙት በካርቱም እና ገዳሪፍ የሚገኙ በትግራይ ስም የተቋቋመውና ሕወሓት በሚዘውረው ኮምዩኒቱ አመራሮች ነው። እነዚህ አመራሮች ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ስም የሚላከውን እና በፖርት ሱዳን የገባውን ሎጂስቲክስ ሀገር ውስጥ ላለው የህወሓት ታጣቂ ለማቀበል ፍላጎት ቢኖራቸውም እየከሰሩ ነው።
ሃገር ቤት ላለው አመራር ሁለት ጊዜ ለማድረስ የተሞከረው መክሸፉን ተከትሎ በተለይም በጻታ፣ በኮረም፣ በዴላ፣ ቦራ አካባቢ ያለው የተራረፈው የሕወሓት ኃይል አሁንም ወደ አማራ ክልል ዋግህምራ ዞን በመግባት እየጣለ ያለውን ዝናብ አሳቻ ሰዓት ጠብቆ እንደከዚህ ቀደሙ የመድሃኒትና እህል ዝርፊያዎች እንዳያከናውን ቀድሞ እየተሰራ መሆኑን ምንጩ ነግረውናል። በዚህም መከላከያው በጻታ፣ በኮረም፣ በዴላ፣ ቦራ፣ አምባ ጉባ፣ ቤርዘባ፣ አዶድዋና ሌሎችም አካባቢዎች የተራረፈውን እና በየሰው ቤት ጭምር ተደብቆ የሚገኘውን የጅንታው ኃይል የማጽዳት ሥራ ጀምሯል። እነጌታቸው ረዳ ከነዚህ አካባቢዎች በመነሳት ወደ አማራ ክልል ጋር የሚያዋስኑ ተራሮች ላይ በመውጣት ኢንተርኔት ሲጠቀሙ መቆእታቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳል አስፋው አብርሃ “የኤርትራ ሰራዊት የድል መረጃ…” በሚል ከምንጬ ሰማው በሚል ባሰራጨው መረጃ፡
ለሽብር ስራ ተልዕኮ ከሱዳን ሃምዳይት ወደ ኤርትራ ኦምሃጀር ሰርጎ ለመግባት የሞከረ 25 አባላት ያሉት የርዝራዡ ቡድን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። በትርጁማንነት የሚሰራ አንድ ጀማል የተባለ ግለሰብም ተይዟል። መረጃውን ያካፈለኝ አንድ የኤርትራ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንን ሲሆን ከተያዙት መካከል ጀማል የተባለው ሰው በርዝራዡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የነበረው ሰው ነው ብሎኛል።” ብሏል።