(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር “የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግራይ ህዝብንና ቤተክርስትያን ከድተዋል” የሚል አደገኛና ከፋፋይ ይዘት ያለው መግለጫ ዛሬ ማውጣቱታቸው ቁጣን ቀስቀሰ።
የትግራይ ሲኖዶስን እናቋቁማለን በሚል እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙት አካላት ጋር እየሰሩ የሚገኙት የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር ዛሬ ያወጡት መግለጫ ቤተክርስቲያንን በመከፋፈል ያሰቡትን ሴራ ለመፈጸም የታለመ ነው ተብሏል።
ሁለቱም በጋራ ባወጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ መከላከያ፣ ኣማራ ልዩ ኃይል፣ ኤርትራ ሰራዊት፣ ሶማሌና ኤምሬትስ በጋራ በትግራይ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋና ወረራ ሲከፍቱ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዝም በምለት የትግራይ ህዝብንና ቤተ ክርስትያንን ከድተዋል”ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።
ሕወሓት በኢትዮጵያ መካለከያ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት መፈጸሙን አምኖ እያለ የሁለቱም መግለጫ ሕዝቡን ለመጠበቅ በትግራይ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱን፣ አስገድዶ መድፈሩን፣ በታንክ ረጋግጦ መግደሉን ያልጠቀሰው የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር መግለጫ የተለያዩ ክልሎች ከሚያስተዳድሩት ሕዝብ ቀንሰው ለትግራይ ሕዝብ የሰጡትን እርዳታ የካደ መግለጫ በማውጣት የትግራይ ሕዝብን ለመነጠል እንዲሁም ቤተክርስቲያንን ለመክፈል እየሰሩ ነው በሚል ተቃውሞ ተነስቷል።
ሕወሓት በትግራይ ክልል ያሉ አምቡላንሶችን ለጦር ሜዳ ማዋሉንና ማውደሙን ተከትሎ በክልሉ ለአስቸኳይ ጊዜ የሚሆን አምቡላንስ በጠፋበት ሰዓት ክልሎች አምቡላንሶችን ለትግራይ ክልል መስጠታቸው ይታወሳል። የተለያዩ እህሎችንም ይዞ በመሄድ ለትግራይ ሕዝብ ያላቸውን ወገንተኝነት አሳይተዋል። ታማኝ በየነን ጨምሮ ሌሎች በሰብአዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ ዜጎች የተለያዩ እርዳታዎችን በማሰባሰብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰጥተዋል። ሆኖም ግን በሕወሓት ጁንታ የሚመሩት የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር ይህንን ሁሉ ክደው የትግራይ ሲኖዶስን ለመመስረት የሚጠርግላቸውን መስመር ለማስፋት የትግራይ ሕዝብና የትግራይ ቤተክርስቲያን ተክዳለች የሚል አደገኛ ጨዋታ መጫወት ጀምረዋል።
በአሁኑ ሰዓትም የትግራይ ሲኖዶስ አጀንዳ በውጭ በሚገኙ የሕወሓት ሚዲያዎች በሰፊው እየተቀነቀነ ይገኛል። ሕወሓት ስልጣን ላይ እያለ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሎ በነበረበት ወቅት በበርካታ ም ዕመናን ጥረት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ወደ ሃገር ቤት በመግባት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲጠነክር በሚደረግበት ወቅት በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት አባይ ጸሐዬ “አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ከሆነ አክሱም ላይ የራሳችንን ሲኖዶስ እናቋቁማለን” ሲሉ በግልጽ መናገራቸው የሚታወስ ነው። አሁን የመቐለ ሀገረስብከት እና የነገረ መለኮት ምሁራን ማሕበር እየሄዱበት ያለበት መንገድ ከአመታት በፊት በሕወሓት እቅድ ውስጥ ተጽፎ የሚገኘውን ንው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሕግን ለማስከበር እያደረገ ባለው ተጋድሎ አባይ ጸሐዬ በርሃ ውስጥ ቀሚስ ለብሶ መገደሉ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ባለፈው ሳምንት ለሰዓታት ባደረገው የማጽዳት ሥራ ሱዳን የሕወሓትን ጥቃት ተገን በማድረግ ከያዘቻቸው የኢትዮጵያ መሬቶች መካከል አንዱን ቀበሌ ማስቅለቀቁ ይታወሳል። ይህ ለሱዳን እንደማስጠንቀቂያ የተፈጽመው ጥቃት ሱዳን ሌሎችንም በሃይል የያዘቻቸውን ቦታዎች እንድትለቅ ቢሆንም፤ ግዛቷን ከኢትዮጵያ በኃይል ከያዘቻቸው ቦታዎች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን መገንባቷን ግን አለማቆሟ ተገለጸ።
ከወር በፊት የሱዳን ጦር በወረራ በያዘው የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን እየገነባ እንደሆነ ከ1 ወር በፊት መግለጹን” የሚያስታውሰው አስፋው አብርሃ “ሸምሱዲን ከባሺ የተባለ የሱዳን ጄኔራል ትናንት የድልድዮቹን የግንባታ ሂደት በቦታው ተገኝቶ ጎብኝቷል።” ሲል ዛሬ መረጃውን ይፋ አድርጓል።
ጄ/ል ሸምሱዲን ካባሺ ከጉብኝቱ በኋላ ” ድልድዮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከተጠናቀቁ በክረምቱ ወቅት የሚደረጉትን የወታደሮቻችንን እንቅስቃሴ የተሳለጠ ያደርጉታል ” ብሏል።
ለዘመናት መቋጫ ሳያገኝ የቆየው በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ከኅዳር ወር መጀመሪያ ወዲህ ሱዳን ይዞታዬ ነው ወዳለቻቸው የድንበር አካቢዎች ወታደሮቿን ካሰማራችና ኢትዮጵያ የሱዳን ሠራዊት ድንበሬን ጥሶ ገብቷል ካለች በኋላ ውጥረቱ አይሏል።
ሁለቱም አገራት ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን ኢትዮጵያ የድንበሩን ጉዳይ በንግግር ለመፍታት እንደምትሻ ነገር ግን በአካባቢው ያለው ሁኔታ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስትጠይቅ፤ ሱዳን ደግሞ ሠራዊቷ ከያዛቸው ቦታዎች እንደማይወጣ በተደጋጋሚ ገልጻለች።