Site icon www.zehabeshanews.com

ጌታቸው ረዳ ለጠ/ሚኒስትሩ 1 ሳምንት ምላሽ ሰጠ

በርከት ያሉ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች በተለያዩ ሃገራት እየተሰጠ ስላለው የኮቭድ 19 ክትባቶች ባለሙያ አቅርበን መረጃ እንድናቀርብ ጠይቀዋል። በዚህ መሰረት በኒዮርክ ከ2017 እስከ ኮቪድ በዓለም ላይ እስከሚሰራጭበት 2020 ድረስ በህክምና ሙያ፤ እንዲሁም በላይቤሪያ ኢቦላ በተከሰተበት ወቅት ከ2001 እስከ 2014 መጨረሻ ያገለፈሉትን ዶ/ር አብይ ሙሉጌታን አበበን በኮቭድ ክትባት ዙሪያ ጠይቀናቸዋል። ዶ/ር አብይ የኮቪድ ክትባቶች ከኢቦላ ክትባቶች ጋር ስላላቸው ንፅጽር፣ ክትባቱን በየጊዜው መከተብ ይኖርብን ይሆን ጭምር ብለን ጠይቀናቸው አብራርተዋል ይመልከቱት።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጽሕፈት ቤት ለጁንታው የሕወሓት አባላት የአንድ ሳምንት የ እጅ ስጡ የመጨረሻ ጊዜ ጥሪ ትናንት ማቅረባቸውን ተከትሎ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በትግራይ ሚዲያ ሃውስ በመውጣት ምላሽ ሰጠ። ካለመስዋዕትነት የሚገኝ ድል የለም ያለው ጌታቸው በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ መ ስዋ ዕትነት እየከፈሉ መሆኑን ገልጿል። በአማራ ክልል ገብተው ጥቃት ስለመሰንዘራቸውም ጌታቸው ተናግሯል። ተከበዋል እየተባለ ስለሚነገረውም ምላሽ ሰጥቷል።

ከወራት በፊት ጌታቸው ረዳ የኤርትራ 11ኛ ፣ 25ኛ ፣ 33ኛ 52ኛ እና 62 ኛ ክፈለጦሮችን ለወሬ ነጋሪ ሳናስቀር ድባቅ መተናቸዋል ሲል ሲናገር የነበረ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሃሳቡን ቀይሮ “እስካሁን በነበረው ጦርነት የኤርትራ ሰራዊት የአቢይን ሰራዊት ከፊት ይማግድ ስለነበር ብዙ ጉዳት አልደረሰበትም።” ሲል ከተናገረ በኋላ በዚህ ሰሞኑ ውጊያ ግን የኤርትራ ሰራዊት ላይ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተነዋል ሲል በቃለምልልሱ ይናገራል።
እስከ ዛሬ ፋኖን በተመለከተ ጥቃት ፈጸመብን ሲል የነበረው ጌታቸው ዛሬ ደግሞ “ፋኖ እዚህ ግባ የሚባል አቅም የለውም’ ሲል ተናግሯል።
ለዘ-ሐበሻ ቤተቦች ግንዛቤ እንዲረዳ ምላሹን በአጭሩ እንዲህ አቅርበነዋል።

Exit mobile version