Site icon www.zehabeshanews.com

በኔዘርላንድሮተርዳም የሚገኘውደብረ መዊ መድሃኔአለም ቤተክርስቲያን፣ ችግርተባብሶመቀጠሉ ተነገረ

በኔዘርላንድ ሮተርዳም የሚገኘው ደብረ መዊ መድሃኔአለም ቤተክርስቲያን፣  ህገወጥ በሆነ መንገድ እራሳቸውን የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አድርገው በሰየሙ ጥቂት ግለሰቦች፣እየታመሰ እንደሆነ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ምዕመናን ለዘሃበሻ ገለጹ።

ይህ ህገወጥ ቡድን አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጽምባት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትን ክብር በሚነካ መልኩ ከመቅደስ እስከማባረር መድረሳቸውን አክለው ገልጸዋል። በትናንትናው እለትም ፖሊስ ወደ ቤተክርስቲያኑ በመጥራት ለረጅም ግዜ ቤተ ክርስቲያኑን ባገለገሉ ካህኑ አባት ላይ አሳፋሪ ድርጊት ፈጽምዋል። ከዚህ ቀደምም ቤተክርስቲያንን እያገለገሉ የሚገኙትን ካህን አባት ቤተክርስቲያን እንዳይመጡ የማስፈራሪያ ደብዳቤ በመጻፍ አሳዛኝ ድርጊት ፈጽመዋል።

በዚህ  የድፍረት ተግባራቸው በመግፋት አጥቢያውን ከአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመነጠል እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ከወራት በፊት ባወጡት መግለጫ መረጋገጡን ምንጫችን አክሎ ገልስጿል።  በቅዱስ ሲኖዶስ ስር ለተቋቋመው፣ የጀርመን እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ባስገቡት የቤተክርስቲያንን ክብር የሚጋፋ ደብዳቤ፣ በመላው ኔዘርላንድ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ድጋፍ የተቋቋመን ቤተክርስቲያን፣ ከእናት ቤተከረስቲያን መዋቀር ውጭ ማድረጋችውን አሳውቀዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ሶኖዶስ ጽህፈት ቤት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ለችግሩ መፍትሄ ይፈልጉ ዘንድ ምዕመናን ጥሪ አቀርበዋል።

Exit mobile version