የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሜሽን የህብረተሰቡን ጥቆማ መሠረት ባደረገው ክትትል (ስድስት ሺህ) 6000 ዶላር በብር አዘጋጅ ብለውኝ ከያዙት ዶላር ከሚያደርጉት የተዘጋጀ ወረቀት ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ። በባህርዳር ከተማ በአንድ ቤት ከውጭ የመጡ ሁለት ላይቤሪያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ህገ ወጥ የዶላር ገንዘብ በማተም ሲያሰራጩ በከተማው በሚኖሩ ግለሰቦች ጥቆማ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውልዋል ።
ከፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሁለቱ ግለሰቡች የምርት ሂድቱን ከአጠናቀቁ በኃላ የሚያሰራጭላቸው ግለስብ ሲፈልጉ እንደነበር መረጃዎችን ያመላክቷል ። በተጨማሪም ጥቆማ የሰጠውን ግለሰብ ከመጀመሪያው እሰከ መጨረሻው የምርት ሂደቱን እንዲከታተል በማድረግ ተባባሪዎቻቸው ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርገዋል ።
ለፖሊስ ምርምራ ክፍል ቃሉን ሲሰጥ “ውሀ ከጨመሩበት በሃላ የሆነ ፓውደር አድርገውበት ከትንሽ ቆይታ በሃላ ወረቀቱን ሲያሹት ባለ 20 እና50ዶላር ሆነ እና ዶላሩ በዚህ መልኩ ነዉ ያለ ላንተ እንሰጥህና ህጋዊ ታደርግልናለህ በብር መቶ ሚሊወን ይሆናል አለኝ ይሄንንም ባንክ ወስደህ ፎርጅድ አለመሆኑን ቸክ አድርግ ብለው ትተውልኝ ሄዱ” የሚል ቃል ሰጥቷል ።
በተጨማሪም “ወደ ድርጅቴ መጠው ኢንቨስት መንት መስራት እንፈልጋለን ሲሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ የት እንደሆነ ነግሬ ሰደድኩአቸው በኃላ ተመልሰው መጠው መረጃ እንደወሰዱና አብረን እንድንሰራ በ ሪል እስቴት ዘርፋ መሰማራት እንደሚፈልጉና የገንዘብ ችግር እንደሌለባቸው እና ገንዘቡ 2.5ሚሊወን ዶላር ኮትድ የሆነ በዲፕሎማት እንዳስገቡና ከኢራን ከነበሩ የአሜሪካን የጦር ቤዝ ዶላሩ መምጣቱን ነግረውኝ ሁለት ሰማያዊ ወረቀት ከኪሳቸው አወጡና ሰሀን እንዳመጣ ጠይቀውኝ ስሰጣቸው ወረቀቱን ከሰሀኑ ላይ አርገው በማለት የሥራቸው ተባባሪ እንድሆነ ጠይቀውኛል የሚል ቃል ሰጥቷል ።
ግለሰቡ ለፖሊስ የሰጠው ጥቆማ ሊበረታታ ይገባዋል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉን ምርመራ ላይ ሲሆን እንደተጠናቀቀ ለህግ እንደሚያቀርበው የተገኘው መረጃ ያመለክታል
ተዋቸውደርሶ