የአውስትራሊያ ኦሮሞ ኮሚኒቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሜልበርን የተቃውሞ ዝግጅት እንዳሰናዳ አስታውቋል፡፡
የተቃውሞው ምክንያት ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ ቦረና የህክምና እርዳታ በመረጡት ሆስፒታል እንዲያገኙ ለመጠየቅ እንደሆነ መግለጫው አስረድቷል፡፡ በዚህ መሰረት ዛሬ የተቃውሞው ዘመቻ እንደሚጀመር አመልክቷል፡፡ ተቃውሞውም ለእስረኞቹ ድጋፍ ለማሳየት ቢጫ ልብስ መልበስንና መኪና ተከራይቶ በሜልበርን ከተማ ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግን እንደሚያካትት መግለጫው ጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ወደሀያ የሚሆኑ የሜልበርን ነዋሪዎች በቪክቶሪያ በሚገኘው የፓርላማው ደጅ ላይ ተቀምጠው ለአርባ ስምንት ሰአታት የረሀብ አድማ እንደሚያደርጉም መግለጫው አስታውቋል፡፡ የዚህ ተቃውሞ ዋና አስተባባሪዎች ፀጋዬ አራርሳ፣ ቶልቱ ቱፋ እና ታረቀኝ ቺምዲ መሆናቸውን ከመግለጫው ላይ ለመመልከት ችለናል፡፡