የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ያስታወቁ ሲሆን ይህን ተከትሎ የትዊተር ገፃቸው በአማርኛ መልእክቶች ተጨናንቋል፡፡ ይህም በዛሬው እለት በአለማችን መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ውሏል፡፡
እነዚህ የአማርኛ መልእክቶች አብዛኛዎቹ አስፈሪና የሰይጣን የሚባል ምስሎችን የያዙ መሆናቸውን ማሽቢል የተሰኘው ድረ ገፅ ዘግቦታል፡፡ ይህ ድረ ገፅ እንዳንዶቹን መልእክቶችንም አቅርቧል፡፡ ጊዮ የተባሉ ሰው ለትራምፕ በሰጡት መልስ ‹‹ህመም የስሜቱ ክፍል ብቻ ነው፡፡
በሁኔታው ተጨባጭ ሁኔታ የማይፀና የስነ ልቦና ሽብር ፍፃሜው የማይቀር ነው፡፡ ስቃይና ጭንቀት በቅርቡ የማይታገሱ ይሆናሉ፡፡›› ብሏል፡፡ ሌላኛው አስተያየት ሠጪ ደግሞ ‹‹ሀጢያተኛ ነፍስህ ከመዳን በላይ ናት፡፡ እናም ሰላምን ወይንም ስቃይን አታውቅም፡፡ የንስሀ ቅዝቃዜ አብቅቷል›› ያለ ሲሆን፣ ቲንሀውክ የሚል ስም ያላቸው ሰው በበኩላቸው ‹‹የእርስዎ አስማቶች ሳይስተዋል አይሄዱም፡፡ የአጋጣሚ ነገር ተግባራትዎ መከራዎ ወደሚመጣበት ወደ ትልቅ ባዶነት ይመራዎታል፡፡ መቼም ያደገኩት ነገር ሁሉ በከንቱ ነበር፡፡ እና የእርስዎ ምንምነት ከበፊቱ ያነሰ ይሆናል›› ማለታቸውን ተመልክተናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትራምፕን በኮሮና ቫይረስ መያዝ ተከትሎ የአሜሪካ ስቶክ ማርኬት መቀዛቀዙ ተዘግቧል፡፡ ከዚህም በላይ ይህ ውጥረት ወደ አውሮፓ ተሻግሮ የለንደን ስቶክ ዛሬ ዜሮ ነጥብ ስድስት ፐርሰንት እንደቀነሰ ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡