የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ባለፉት አስር አመታት የሰብአዊ መብትን ለሚጥሱ አገራት ከ16 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ የሚያወጣ ጦር መሳሪያ መሸጡን አንድ ጥናት ይፋ አደረገ፡፡ እንደጥናቱ ከሆነ ፍሪደም ሀውስ በተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰትን እንደሚፈፅሙ ከተዘረዘሩ 49 አገራት ውስጥ ለ36ቱ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት መሳሪያ ሸጦላቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ ከ2010 እስከ 2019 ድረስ መሳሪያው ከተሸጠላቸው ከእነዚህ አገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያም አለችበት፡፡ ጥናቱ በተጠቀሰው አመታት ውስጥ እንግሊዝ ወደ ሁለት ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ ጦር መሳሪያ ለኢትዮጵያ መሸጧን አስረድቷል፡፡