Site icon www.zehabeshanews.com

ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያን ጉሮሮ በቀናት ውስጥ እዘጋለሁ በሚል የኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሆነውን ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ።

በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ወደ ሚሌ በባቲ መስመር እንዲሁም በጭፍራ በኩል በ2 አቅጣጫ ቆርጦ ለመሄድ ያለ የሌለ ሃይሉን ለወራት ገብሯል። ለደጋፊዎቹም ትናንት አርብ ይህን ሚሌን እቆጣጠራሉ ብሎ በድፍረት ሲናገር የነበረው ሕወሓት ድል ሲርቀው ሚሌን እንደተቆጣጠረ አድርጎ ሃሰተኛ መረጃዎችን ዛሬ ማሰራጨቱን ቀጥሏል።

በጭፍራ መስመር ውጊያ ከፍቶ ወደ ሚሌ ሊገሰገስ የነበረው የሕወሓት ኃይል በአፋር ተዋጊዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መመታቱን የገለጹት ምንጮቹ፤ በካሳጊታም አድርጎ ሚሌን አልሞ የመጣው ሕወሓት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በየቀኑ ሙከራዎችን ቢያድርግም ኃይሉን ለሞት ከማስገበር ውጭ ምንም ድል እንዳላገኘ ተገልጿል። ይህ ያልተሳካለት የሕወሓት ታጣቂ በባቲ ገርፋ መስመር አድርጎ በደዌ ወረዳ በመግባት በደዌ በከለላት አካባቢም አዲስ ግንባር በመፍጠር የኢትዮጵያ ኃይሎችን ለመቁረጥ ያደረገው ጥረት ከሽፎ የተደመሰሰው ተደም ሰሶ የቀረው ወደኋላ መመለሱን ምንጮች ከዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። በዚህ አካባቢም በአጠቃላይ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ የሕውሓት ታጣቂዎች እጃቸውን ለኢትዮጵያ ኃይሎች ሰጥተዋል።

ሕወሃት በተለያዩ ከተሞችን ሲቆጣተር እስር ቤት ያሉ በወንጀል የተጠረጠሩና የታሰሩ ሰዎችን በመልቀቅ ወደ ጦርነት ግንባር እንደሚወስዳቸው፣ ሲፈልገው ጥይት ማብረጃ፣ ሲፈልገው ምሽግ ቆፋሪ፣ ሲፈልገው ደግሞ ከአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የተሰራ የኢትዮጵያ እና የአማራ ልዩ ኃይል ዩኒፎርም በማስለበስ ልክ እንደምርኮኛ አድርጎ አስጠንቶ በቴሌቭዥን እንደሚያሳያቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በዚህ በአፋር መስመርም ሚሌን ለመያዝ ከባቲ፣ ኮምቦልቻ እና ከደሴ እስር ቤቶች የተለቀቁ እስረረኞችን ለጥይት ማብረጃ ከፊትለፊት እንዳሰለፋቸው ተሰምቷል።

Exit mobile version